ገላን ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል

ገላን ከተማ ወደ ከፍተኛ ሊግ ያሳደገውን አሰልጣኝ ዳግም ወደ ክለቡ ተመልሷል።

በከፍተኛ ሊጉ ያለፉትን ሦስት ዓመታት ጥሩ ተፎካካሪ በመሆን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለመግባት እየታተረ የሚገኘው ገላን ከተማ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በአሠልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ ሲመራ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ከአሠልጣኙ ጋር መለያየቱን ተከትሎ የቀድሞ አሰልጣኙ ዳዊት ታደለን በድጋሚ ወደ ቡድኑ መልሶታል። አሰልጣኝ ዳዊት አብረውት የሚሰሩ ተጫዋቾችንም 

የቀድሞ የአዳማ ከተማ ወጣት ቡድኖች አሰልጣኝ ዳዊት በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በአቃቂ ቃሊቲ ጥሩ ጊዜ ባያሳልፍም ከዚህ ቀደም ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ (በቀድሞ አጠራሩ ብሔራዊ ሊግ) እና ገላን ከተማን ወደ ከፍተኛ ሊግ በማሳደግ ይታወቃል።

ያጋሩ