ከሰዓታት በኋላ ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን የሚያደርገው የባንክ አሰላለፍ ታውቋል

7 ሰዓት ሲል ከዛንዚባሩ ኒው ጄኔሬሽን ጋር የቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታውን የሚያደርገውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ ታውቋል።

በኬንያ አስተናጋጅነት እየተከናወነ የሚገኘው የሴካፋ ዞን የአፍሪካ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ የማጣሪያ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎችን በትናንትናው ዕለት ማስተናገድ ጀምሯል። በምድብ ሁለት ከቪሂጋ ኩዊንስ፣ ኒው ጄኔሬሽን እና ዪይ ጆይንት ስታርስ ጋር የተደለደለው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክም እሁድ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጎ ድል መቀዳጀቱ ይታወሳል። ዛሬ ሰባት ሰዓት ደግሞ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታውን ከኒው ጄኔሬሽን የሚያደርግ ይሆናል። ሶከር ኢትዮጵያም ቡድኑ በጨዋታው የሚጠቀመውን አሰላለፍ ቀድማ አግኝታለች። አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛውም ከእሁዱ ጨዋታ ታሪኳ ዴቢሶ እና እመቤት አዲሱን አሳርፈው ዓለምነሽ ገረመው እና የምስራች ላቀውን ወደ መጀመርያ አሰላለፍ አምጥተዋል።

ግብ ጠባቂ

ታሪኳ በርገና

ተከላካዮች

ብዙዓየሁ ታደሰ
ሀሳቤ ሙሶ
ትዝታ ኃይለሚካኤል
ዓለምነሽ ገረመው

አማካዮች

ሕይወት ደንጊሶ
አረጋሽ ካልሳ
ሰናይት ቦጋለ

አጥቂዎች

የምስራች ላቀው
መዲና ዐወል
ሎዛ አበራ

ያጋሩ