ወልቂጤ ከተማ አዲስ ምክትል አሠልጣኝ ቀጥሯል

በአሠልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው የሚመሩት ወልቂጤ ከተማዎች አዲስ ምክትል አሠልጣኝ ሾመዋል።

የትግራይ ክልል ክለቦችን ለመተካት በተደረገው ውድድር በሊጉ መክረማቸውን ያረጋገጡት ወልቂጤ ከተማዎች አረፋፍደውም ቢሆን ቡድናቸውን እያጠናከሩ እንደሆነ ይታወቃል። ሶከር ኢትዮጵያ ዛሬ እንዳስነበበችው ክለቡ አይቮሪኮስታዊው የግብ ዘብ ጉልስጎኖን ሲላቫይን ጎቦሆ አስፈርሟል። አሁን በተገኘ መረጃ ደግሞ የአሠልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ሁለተኛ ምክትል የሚሆን አሠልጣኝ መሾሙን ይጠቁማል።

ሁለተኛ ምክትል በመሆን ቡድኑን የተቀላቀሉት አሠልጣኝ ኢዮብ ማለ ናቸው። የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ፣ ሀዲያ ሆሳዕና፣ ሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን እና ጌዲኦ ዲላ አሠልጣኝ የነበሩት ኢዮብ ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ በፕሪምየር ሊጉ ብቅ የሚሉበት ዕድል መፈጠሩን ወልቂጤ ከተማ ሥራ አስኪያጅ አቶ ታምራት ለሶከር ኢትዮጽያ ገልፀዋል፡፡

ያጋሩ