በአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው መከላከያ ከደቂቃዎች በፊት ጋናዊውን አጥቂ አስፈርሟል።
አዲሱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለብ መከላከያ ዳግም በሊጉ መሳተፉን ካረጋገጠ በኋላ ስብስቡን ሲያጠናክር ከርሟል። ከሳምንታት በፊት የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ቢሾፍቱ ላይ የጀመረው ክለቡም ከደቂቃዎች በፊት ጋናዊ የአጥቂ መስመር ተጫዋች በይፋ ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
ክለቡን በአንድ ዓመት ውል የተቀላቀለው ተጫዋች ኢማኑኤል ኦኩቱ ነው። በጋና አክራ የተወለደው የ28 ዓመቱ አጥቂ አብዛኛውን የእግርኳስ ህይወቱን በዛምቢያ ሊግ አሳልፏል። በተለይ ለካብዌ ዋሪየርስ፣ ዛናኮ እና ለብዩልድኮን ክለቦች ለአንድ አንድ ዓመት ግልጋሎት ሰጥቷል። ወደ መከላከያ የሚያደርገውን ዝውውር ለመቋጨት ትናንት ምሽት 2:50 አዲስ አበባ የደረሰው ተጫዋቹም ከደቂቃዎች በፊት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በመገኘት ለመከላከያ ፊርማ ማኖሩ ታውቋል።