ዛሬ ምሽት ከጋና ጋር የሚጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ አሰላለፍ ታውቋል።
ኳታር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ ለዛሬ ጀምሮ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታውን የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት ከጋና አቻው ጋር በኬፕ ኮስት ስታዲየም ሲጫወት የሚጠቀመውን የመጀመሪያ አሰላለፍ ሶከር ኢትዮጵያ አግኝታለች።
የዛሬው አሰላለፍ ይህንን ይመስላል
ግብ ጠባቂ
ተክለማርያም ሻንቆ
ተከላካዮች
አሥራት ቱንጆ
ያሬድ ባየህ
አስቻለው ታመነ
ረመዳን የሱፍ
አማካዮች
ይሁን እንደሻው
ታፈሰ ሰለሞን
ሽመልስ በቀለ
አጥቂዎች
አቡበከር ናስር
ጌታነህ ከበደ
አማኑኤል ገብረሚካኤል