ዋልያውን የሚገጥመው የጋና አሰላለፍ ታውቋል

ምሽት አራት ሰዓት ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥመው የጋና ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ አሰላለፍ ታውቋል።

ኳታር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በአሠልጣኝ ቻርለስ አኮኖር የሚመራው የጋና ብሔራዊ ቡድን ምሽት አራት ሰዓት ላይ የምድብ የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታውን ከኢትዮጵያ አቻው ጋር ያደርጋል። ጨዋታው ሊጀመር በርከት ያሉ ሰዓታት ቢቀሩትም የጋና ብዙሃን መገናኛዎች የብሔራዊ ቡድናቸው የመጀመሪያ አሰላለፍ መታወቁን እየዘገቡ ይገኛሉ።

ግብ ጠባቂ

ሪቻርድ ኦፎሪ

ተከላካዮች

አንዲ ይያዶም
ዳንኤል አማርቲ
አሌክሳንደር ጂኩ
ባባ ራህማ

አማካዮች

ባባ ኢድሪሱ
ሙባረክ ዋካሶ
ጄፍሪ ሽሉፕ
ካማልዲን ሱሌይማና

አጥቂዎች

አንድሬ አይው
ጆርዳን አይው