በኢትዮጵያ እና ዚምባብዌ መካከል የሚደረገውን ጨዋታ ለመከታተል ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ይገባሉ የሚለው ጉዳይ ላይ ውሳኔ ተላልፏል።
ነገ 10 ሰዓት በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም በኢትዮጵያ እና ዚምባቡዌ መካከል የሚደረገው የዓለም ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ላይ የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን በጠበቀ ሁኔታ ውስን ደጋፊዎች ወደ ሜዳ እንዲገቡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለካፍ ደብዳቤ መፃፉ ይታወቃል። ፌዴሬሽኑ ያቀረበውን ጥያቄን ተከትሎ ካፍ ምላሽ መስጠቱን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በዚህም ካፍ በፌዴሬሽኑ የቀረበውን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ በማድረግ በጨዋታው ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም እንዳይገቡ ውሳኔ አስተላልፏል። ይህንን ተከትሎም ጨዋታውን ፍቃድ ያላቸው የብዙሃን መገናኛ አባላት ብቻ በስታዲየሙ ተገኝተው የሚከታተሉት ይሆናል።