ሲዳማ ቡና ግብጠባቂ አስፈርሟል

አስቀድሞ ወደ ሀድያ ሆሳዕና አምርቶ የነበረው ግብጠባቂ ለሲዳማ ቡና ፈርሟል።

በአሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ እየተመራ መቀመጫ ከተማው በሆነችው ሀዋሳ ከተማ ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው ሲዳማ ቡና ግብጠባቂውን መክብብ ደገፋን ለሁለት ዓመት አስፈርሟል።

ለሀድያ ሆሳዕና መፈረሙን ከዚህ ቀደም ዘግበን የነበረው መክብብ በትናንትናው ዕለት ፌዴሬሽን በመገኘት ለሲዳማ ፊርማውን አኑሯል። ከዚህ ቀደም በሀዋሳ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ደቡብ ፖሊስ፣ ሀምበሪቾ እና ሌሎች ክለቦች የተጫወተው መክብብ በዘንድሮ ዓመት በወላይታ ድቻ ዘንድሮ ጥሩ አገልግሎት መስጠቱ ይታወሳል።

ያጋሩ