ወልቂጤ ከተማ ተጨማሪ ተጫዋቾች አስፈርሟል

ወልቂጤ ከተማ የአማካይ እና አጥቂ ስፍራ ተጫዋቾችን አስፈርሟል።

ጫላ ተሺታ ከፈራሚዎቹ አንዱ ነው። በሻሸመኔ ከተማ፣ ሰበታ ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ ሲዳማ ቡና እንዲሁም በ2012 በወልቂጤ ከተማ የተጫወተው የመስመር አጥቂው በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ወደ ሲዳማ ቡና አምርቶ እስከ አጋማሽ ድረስ ቆይታ አድርጓል። አሁን ደግሞ ድንቅ ጊዜ ወዳሳለፈበት ወልቂጤ ከተማ የሚመልሰውን ዝውውር አከናውኗል።

ሌላው ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋች ፍፁም ግርማ ነው። የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ በወልቂጤ ከተማ ወጣት ቡድን እና በኢኮሥኮ የተጫወተ ሲሆን በቀጣዩ የውድድር ዓመት በሠራተኞቹ ማልያ ለመታየት ፊርማውን አኑሯል።

ሦስተኛው ፈራሚ አላዛር ዘውዱ ነው። ዘንድሮ በዲላ ያሳለፈውና በከፍተኛ ሊግ ጥሩ ዓመት ካሳለፉ አጥቂዎች አንዱ የሆነው የቀድሞው የሰሎዳ ዓድዋ፣ ኤሌክትሪክ፣ አዲስ አበባ እና ጌዲኦ ዲላ ተጫዋች በአንድ ዓመት ውል ክለቡን ተቀላቅሏል።

ወልቂጤ እነዚህን ጨምሮ በዝውውር መስኮቱ ስድስት አዲስ ተጫዋቾች ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

ያጋሩ