ንግድ ባንክ በፍፃሜው ጨዋታ የሚጠቀመው አሰላለፍ ታውቋል

ከሰዓታት በኋላ ከኬንያው ቪሂጋ ኩዊንስ ጋር የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን የማጣሪያ የፍፃሜ ጨዋታ የሚያደርገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመሪያ አሰላለፍን ሶከር ኢትዮጵያ አግኝታለች።

በአሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው የአፍሪካ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ከፊቱ አንድ ጨዋታ ብቻ እንደቀረው ይታወቃል። ቡድኑም ከሰዓታት በኋላ (10:00) በዞኑ የፍፃሜ ጨዋታ የኬንያውን ቪኒጋ ኩዊንስ ገጥሞ የሚያሸንፍ ከሆነ ወደ ግብፅ የሚወስደውን ትኬት ይቆርጣል። በዚህ ወሳኝ ጨዋታ አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚጠቀሙትን የመጀመሪያ አሰላለፍንም ድረ-ገፃች አግኝታለች።

በዛሬው ጨዋታ አሠልጣኝ ብርሃኑ ታሪኳ ዴቢሶ እና ትዕግስት ያደታን በማሳረፍ በምትካቸው ዓለምነሽ ገረመው እና ሕይወት ደንጊሶ ወደ አሰላለፍ አምጥተዋል።

ግብ ጠባቂ

ታሪኳ በርገና

ተከላካዮች

ዓለምነሽ ገረመው
ሀሳቤ ሙሶ
ትዝታ ኃይለሚካኤል
ብዙዓየሁ ታደሰ

አማካዮች

ሕይወት ደንጊሶ
እመቤት አዲሱ
ሰናይት ቦጋለ

አጥቂዎች

አረጋሽ ካልሳ
መዲና ዐወል
ሎዛ አበራ

ያጋሩ