ወጣቱ አጥቂ ጅማ አባጅፋርን ለመቀላቀል ተስማምቷል

ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርገው ዝውውር የከሸፈበት ወጣቱ አጥቂ መዳረሺያውን ጅማ ለማድረግ ስምምነት ፈፅሟል።

ከኢትዮጵያ መድህን የወጣት ቡድን ተገኝቶ ዋናውን ቡድን ያገለገለው ወጣቱ አጥቂ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይዘዋወራል ተብሎ ቢጠበቅም ዝውውሩ ሳጥሳካ ቀርቶ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። ተጫዋቹ ወደ ፈረሰኞቹ የሚያደርገው ዝውውር ሳይሳካ መቅረቱን ተከትሎ ወደሌላኛው የመዲናው ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ሊያመራ ይችላል ተብሎ ቢጠበቅም ጉዞው ወደ ጅማ አባጅፋር መሆኑ ታውቋል።

ከኢትዮጵያ መድህን ጋር ውል ያለው ተጫዋቹ የውል ማፍረሺያው 500 ሺ ብር እንደሆነ ሲገለፅ መክረሙ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎም ጅማ የሚጠበቀውን ክፍያ ለመፈፀም ፍቃደኛ በመሆኑ የተጫዋቾ ዝውውር እውን ለመሆን ተቃርቧል። እርግጥ ተጫዋቹ በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ተገኝቶ ፊርማውን ባያኖርም ከክለቡ ጋር በሁሉም መስፈርቶች መስማማቱን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ያጋሩ