የከፍተኛ ሊጉ የምድብ ለ ተወዳዳሪው ሀላባ ከተማ የቀድሞው አሰልጣኙን በድጋሚ ሾሟል፡፡
የ2013 የውድድር አመትን በከፍተኛ ሊጉ ምድብ ለ ስር ታቅፎ ሲወዳደር የነበረው ሀላባ ከተማ በ33 ነጥቦች አራተኛ ደረጃን በመያዝ በአሰልጣኝ ደረጀ በላይ መሪነት ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ለቀጣዩ የ2014 የውድድር ዘመን በድጋሚ ተጠናክሮ ለመቅረብ ያሰበው ክለቡ የቀድሞው አሰልጣኙ አላምረው መስቀሌን በአንድ ዓመት ውል ቀጥሯል፡፡
ከዚህ ቀደም ሀላባ ከተማን ጨምሮ ሻሸመኔ ከተማን አሰልጣኖ ማለፍ የቻለው አሰልጣኙ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በሀላባ ከተማ የአሰልጣኝ ደረጀ በላይ ረዳት በመሆን ያገለገለ ሲሆን ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ደግሞ በድጋሚ ክለቡን በዋና አሰልጣኝነት እንዲመራ መሾሙን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፈይዱ ፍቃዱ ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግረዋል፡፡