አዞዎቹ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አስፈርመዋል

አርባምንጭ ከተማ ከከፍተኛ ሊግ የተከላካይ አማካይ አስፈረመ፡፡

አዲሱ የፕሪምየር ሊግ ተካፋዩ አርባምንጭ ከተማ በትላንትናው ዕለት ኬኒያዊውን የመሀል ተከላካይ ኦቼንግን የክለቡ ስድስተኛ ፈራሚ አድርጎ አስፈርሞ የነበረው አርባምንጭ ከተማ ሰባተኛ አዲስ ፈራሚው በማድረግ አቡበከር ሻሚልን በአንድ ዓመት ውል አስፈርሟል፡፡

ከኢትዮጵያ ቡና የተስፋ ቡድን የተገኘው ይህ የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች በመቀጠል በአዲስ አበባ ዲቪዚዮን ተሳታፊ በሆኑት አዲስ አበባ ፖሊስ እና አዲስ ከተማ ክፍለከተማ በመጫወት ካሳለፈ በኋላ ነበር ወደ ከፍተኛ ሊጉ ተካፋይ ኮልፌ ቀራኒዮ በማምራት የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት ያሳለፈ ሲሆን በቀጣይ ማረፊያውን አርባምንጭ ከተማ ማድረጉ እርግጥ ሆኗል፡፡

ያጋሩ