ከዐፄዎቹ ጋር ወደ ሱዳን የሚጓዙ ተጫዋቾች ታውቀዋል

በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከሱዳኑ አል ሂላል ጋር የመልስ ጨዋታውን የፊታችን እሁድ የሚያደርገው ፋሲል ከነማ ወደ ስፍራው ሲያቀና ይዟቸው የሚሄዳቸውን ተጫዋቾች ዝርዝር ሶከር ኢትዮጵያ አግኝታለች።

የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊ ፋሲል ከነማ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ማለፍ እንደሚጠበቅበት ይታወቃል። ክለቡም የመጀመሪያ ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሱዳኑ አል ሂላል ጋር ባሳለፍነው እሁድ አከናውኖ ሁለት አቻ የተለያየ ሲሆን የመልስ ጨዋታውን ደግሞ የፊታችን እሁድ ኡንዱርማን ላይ ያደርጋል። ክለቡ ወሳኙን ጨዋታ ለማድረግ ወደ ስፍራው ሲያመራ ይዟቸው የሚሄዳቸው 20 ተጫዋቾችን ዝርዝርም ድረ-ገፃችን አውቃለች።

ግብ ጠባቂዎች

ሚኬል ሳማኪ፣ ቴዎድሮስ ጌትነት እና ይድነቃቸው ኪዳኔ

ተከላካዮች

ያሬድ ባየህ፣ ከድር ኩሊባሊ፣ አስቻለው ታመነ፣ አምሳሉ ጥላሁን፣ ሰዒድ ሀሰን፣ አብዱልከሪም መሐመድ እና ሳሙኤል ዮሐንስ

አማካዮች

ሀብታሙ ተከስተ፣ ይሁን እንዳሻው፣ በዛብህ መለዮ፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ በረከት ደስታ እና ናትናኤል ገብረጊዮርጊስ

አጥቂዎች

ኦኪኪ አፎላቢ፣ ፍቃዱ ዓለሙ፣ ዓለምብርሃን ይግዛው እና ሽመክት ጉግሳ

ያጋሩ