ከመስከርም አጋማሽ ጀምሮ በሚካሄደው የመዲናዋ ትልቁ ዋንጫ ላይ ወልቂጤ ከተማ ከውድድሩ ውጭ በመሆኑ በምትኩ አንድ አዲስ ቡድን ተሳታፊ ይሆናል።
ለ15ኛ ጊዜ የሚዘጋጀው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር ከመስከረም አስራ አምስት ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት ስምንት ቡድኖችን በማሳተፍ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚደረግ ይታወቃል። ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ አዲስ አበባ ከተማ፣ መከላከያ፣ አዳማ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ ተጋባዡን የደቡብ ሱዳን ክለብ ሙኑኪ ኤፍ ሲ’ን ጨምረው የመካፈላቸው ነገር እርግጥ ሆኗል። ሆኖም ወልቂጤ ከተማ በውድድሩ ላይ ይሳተፋል ቢባልም ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከዛሬው የዕጣ ማውጣት ፕሮግራም ውጭ ሆኗል።
በዚህም መሠረት አወዳዳሪው አካል በምትኩ የ2013 የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሆነው ፋሲል ከነማን ተካፋይ እንደሚያደርግ ሶከር ኢትዮጵያ በቤስት ዌስተርን ሆቴል ተገኝነተን አረጋግጠናል።
ከደቂቃዎች በኋላ የምድብ ድልድሉ በደማቅ ሁኔታ ይፋ የሚሆን ሲሆን
ይህንንም ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።