አቡበከር ናስር በመጀመርያ አሰላለፍ ለምን አልተካተተም ?

በኮፌዴሬሽን ካፕ የመልስ ጨዋታ ዩአርኤን የሚገጥመው ኢትዮጵያ ቡና አቡበከርን ያልተጠቀመበት ምክንያት ምን ይሆን ?

ኢትዮጵያ ቡና የዛሬ ሳምንት ዩጋንድ አቅንቶ በዩአርኤ በጠባብ ውጤት 2-1 ተሸንፎ መመለሱ ይታወሳል። ውጤቱን የመቀልበስ ግዴታ ውስጥ በመግባት በባህር ዳር የመልሱን ጨዋታ የሚያደርገው ኢትዮጵያ ቡና በአሰላለፉ ውስጥ አቡበከርን እንደማይጠቀም ተረጋግጧል። በተጠባባቂ ወንበር ላይ የምንመለከተውም ይሆኗል።

ባልተለመደ ሁኔታ አቡበከር ተቀያሪ መሆኑ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ለማጣራት ባደረግነው ጥረት ክለቡ ማረጋገጫ ባይሰጥም ከጨዋታ መደራረብ ጋር ተያይዞ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበት እንደሆነ ሲነገር ከጨዋታው ክብደት አንፃር መድሀኒት ወስዶ ተቀይሮ እንዲገባ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ሰምተናል።

የኢትዮጵያ ቡና እና ዩአርኤ ጨዋታ ዘጠኝ ሰዓት ሲል የሚጀመር ይሆናል።

ያጋሩ