አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለሀያ አምስት ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል

በዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣርያ ላይ እየተካፈለ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለቀጣይ ሁለት ጨዋታዎች ዝግጅት ለተጫዋቾች ጥሪ አድርጓል፡፡

ከዚምባብዌ ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ ጋር ተደልድሎ ሁለት ጨዋታዎችን በማድረግ ሦስት ነጥብ የያዘው ብሔራዊ ቡድኑ በመጪው መስከረም 26 እና መስከረም 30 ከደቡብ አፍሪካ ጋር በሜዳው እና ከሜዳው ውጪ ለሚያርጋቸው ተከታታይ ጨዋታዎች 25 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጎላቸዋል። ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች የፊታችን ዕሮብ መስከረም 12 በጁፒተር ሆቴል በመሰባሰብ ለአጠቃላይ የቡድኑ አባላት የጤና ምርመራዎች ከተደረጉ በኋላ ዝግጅታቸውን ከመስከረም 14 ጀምሮ በባሕር ዳር ከተማ የሚያከናውኑ ይሆናል።

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

ፋሲል ገ/ሚካኤል (ባህር ዳር ከተማ)፣ ተክለማርያም ሻንቆ (ሲዳማ ቡና) እና ጀማል ጣሰው (አዳማ ከተማ)

ተከላካዮች

መናፍ ዐወል (ባህር ዳር ከተማ)፣ ያሬድ ባዬ ( ፋሲል ከነማ)፣ አስቻለው ታመነ (ፋሲል ከነማ)፣ ደስታ ዮሐንስ (አዳማ ከተማ)፣ ሱሌይማን ሀሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ረመዳን የሱፍ (ወልቂጤ ከተማ)፣ አሥራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና) እና ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

አማካዮች

መስዑድ መሐመድ (ጅማ አባጅፋር)፣ አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ታፈሰ ሰለሞን (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ይሁን እንደሻው (ፋሲል ከነማ)፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)፣ ሽመልስ በቀለ (ኤልጎውና)

አጥቂዎች

ሽመክት ጉግሳ (ፋሲል ከነማ)፣ አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና)፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ጌታነህ ከበደ (-)፣ አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ቸርነት ጉግሳ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)