የሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰላለፍ ታውቋል

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የሚጠቀምበት አሰላለፍ ይፋ ሆኗል።

በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚመራው ከ20 ዓመት ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ ማጣርያ ሩዋንዳን ለመግጠም ኪጋሊ የሚገኝ ሲሆን በ10፡00 ለሚያደርጉት ጨዋታ የሚጠቀሙበትን አሰላለፍ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

ግብ ጠባቂ
እየሩሳሌም ሎራቶ 

ተከላካዮች 

ብዙዓየሁ ታደሰ – ብርቄ አማረ – ቤተልሔም በቀለ – ናርዶስ ጌትነት (አ)

አማካዮች

ማዕድን ሳህሉ – ገነት ኃይሉ – መሳይ ተመስገን  

አጥቂዎች

አረጋሽ ካልሳ – ቱሪስት ለማ – ረድኤት አስረሳኸኝ

ያጋሩ