ወልቂጤ ከተማ ከተከላካዩ ጋር በስምምነት ተለያይቷል

ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከሰራተኞቹ ጋር ያሳለፈው የመሐል ተከላካይ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

2012 ላይ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ዋናው የሀገሪቱ የሊግ እርከን ያደገው ወልቂጤ ከተማ ባደገበት ዓመት የመሐል ተከላካዩን ቶማስ ስምረቱ ከኢትዮጵያ ቡና አስፈርሞ እንደነበር ይታወሳል። ተከላካዩ በኮቪድ-19 ምክንያት የተሰረዘውን ግማሽ እና የ2013 የውድድር ዓመትን በክለቡ በመቆየት ግልጋሎት ሲሰጥ ነበር።

ከስፖርተኛ ቤተሰብ የተገኘው ቶማስ ዓምና ከሠራተኞቹ ጋር የሚያቆየውን የሁለት ዓመት ውል ፈርሞ አንድ ዓመት በክለቡ ቢቆይም በዛሬው ዕለት በስምምነት መለያየቱ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች። የቀድሞ የሱሉልታ፣ ወላይታ ዲቻ እና ኢትዮጵያ ቡና ተከላካይ ከሌሎች የሊጉ ክለቦች ጋር ድርድር እያደረገ መሆኑን ስንረዳ በሁለት ቀናት ውስጥም ማረፊያው እንደሚለይ ታውቋል።