ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ቲፒ ማዜምቤ : ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ቅዱስ ጊዮርጊስ 2-2 ቲፒ ማዜምቤ

11′ በሃይሉ አሰፋ ፣ 59’አዳነ ግርማ — 45+2′ ዳንኤል አድጄል ፣ 46′ አስቻለው ታመነ (በራሱ ግብ ላይ)

ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ከሶከር አትዮጵያ

ተጠናቀቀ
ጨዋታው 2-2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

90′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ራምኬል ወጥቶ ጎድዊን ቺካ ገብቷል፡፡

90′ የተጫዋች ለውጥ – ቲፒ ማዜምቤ
ክርስቲያን ሊዩንዱማ ገብቶ ጆናታን ቦሊንጊ ወጥቷል

85′ የተጫዋች ለውጥ – ቲፒ ማዜምቤ
አዳማ ትራኦሬ ወጥቶ ጊቭን ሲንጉሉማ ገብቷል፡፡

76′ አዳማ ትራኦሬ ከርቀት የመታው ኳስ በግቡ አናት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

74′ ከአዳነ በረጅሙ የተላከው ኳስ በሃይሉ እና ግብ ጠባቂውን ቢያገናኝም የመታው ኳስ ተመልሶበታል፡፡

70′ ሮጀር አሳሌ የመታውን ጠንካራ ኳስ ኦዶንካራ አውጥቶበታል፡፡

68′ የተጫዋች ለውጥ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ተስፋዬ አለባቸው ወጥቶ ምንተስኖት አዳነ ገብቷል፡፡

62′ የተጫዋች ለውጥ – ቲፒ ማዜምቤ
ሮጀር አሳሌ ገብቶቶማስ ኡሌዌንጉ ወጥቷል፡፡

59′ ጎልልል
ከበሃይሉ የተሻገረውን ቅጣት ምት ተጠቅሞ አዳነ ግርማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አቻ አድርጓል፡፡

56′ ተስፋዬ አለባቸው ከርቀት የሞከረው ኳስ ኢላማውነን ስቶ ወጥቷል፡፡

50′ ራምከኬል ሎክ ከርቀት የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው በቀላሉ ይዞታል፡፡

46′ ጎልልል
አስቻለው በራሱ ግብ ላይ አስቆጠረ

ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ ተጀመረ

ሁለቱም ቡድኖች ከመልበሻ ክፍል ወጥተዋል፡፡
——–
በስታድየሙ ያለው ኔትዎርክ ለስራችን እክል እየፈጠረ ይገኛል፡፡ በዚህም ምክንያት ፅሁፎች የሚዘገዩት በኔትዎርክ ምክንያት መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
——–

ተጠናቀቀ
የመጀመርያው አጋማሽ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

45+2 ጎልልል
ዳንኤል አድጄል ቲፒ ማዜምቤን አቻ አድርጓል፡፡

45′ የመጀመርያው 45 ተጠናቆ 2 ደቂቃ ተጨመረ

42′ ዳንኤል አድጄል ከቀኝ መስመር የሞከረው ኳስ ኢላማውን ሳያገኝ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

38′ ሮበርት ኦዶንካራ ጉዳት አጋጥሞታል፡፡ አሁን የህክምና እርዳታ ተደርጎለት ወደ ጨዋታ ተመልሷል፡፡

35′ ጨዋታው ፈጣን እና ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየታየበት ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በበሃይሉ እና ራምኬል ፍጥነት ለመጠቀም ሲጥር ቲፒ ማዜምቤዎች ለጆናታን ያልተሳኩ ረጃጅም ኳሶችን በመጣል የግብ እድል ለመፍጠር እየሞከሩ ይገኛሉ፡፡

30′ ቶማስ ኢሉሙንጉ የመታውን ኳስ ኦዶንካራ በቀላሉ ይዞበታል፡፡

23’ቢጫ ካርድ
የጆኤል ኪምዋኪ የመጀመርያውን የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመልክቷል፡፡

ጎልልል!!!!
11′ በሃይሉ አሰፋ ከፍፁም ቅጣተ ትምት ክልል ውጪ መትቶ በግሩም ሁኔታ የቅዱስ ጊዮርጊስን ቀዳሚ ጎል ከመረብ አሳርፏል፡፡

1′ ጆኤል ካሱሱላ የመታው ቅጣት ምት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ
ጨዋታው በቅዱስ ጊዮርጊስ ጀማሪነት ተጀምሯል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቀኝ ወደ ግራ ፣ ማዜምቤ ከግራ ወደ ቀኝ ያጠቃሉ፡፡

09:42 ተጫዋቾች እና ዳኞች ሰውነታቸውን አፍታተው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

09:20 ሁለቱም ቡድኖች ሜዳ በመግባት ሰውነታቸውን ማፍታታት ጀምረዋል፡፡

soccer-4-icon

አሰላለፍ

ቅዱስ ጊዮርጊስ

ሮበርት ኦዶንግካራ

አሉላ ግርማ – አይዛክ ኢሴንዴ – አስቻለው ታመነ – መሃሪ መና

ምንያህል ተሾመ – ተስፋዬ አለባቸው – ናትናኤል ዘለቀ

በሃይሉ አሰፋ – አዳነ ግርማ (አምበል) – ራምኬል ሎክ

ተጠባባቂዎች

ዘሪሁን ታደለ ፣ ደጉ ደበበ ፣ አበባው ቡታቆ ፣ ቢያድግልኝ ኤልያስ ፣ ምንተስኖስት አዳነ ፣ ጎድዊን ቺካ ፣ አቡበከር ሳኒ

 

ቲፒ ማዜምቤ

ጆኤል ኪምዋኪ – ጂያን ካሱሱላ – ሳሊፍ ኩሊባሊ – ሜሪቪሌ ቦፔ – አዳማ ትራኦሬ – ካባሶ ቾንጎ – ዳንኤል አድጄል – ሲልቪያን ግቦሆ – ቶማስ ኡሊንዌንጉ – ክርስቲያን ኮፊ – ጆናታን ቦሊንጊ

 

*ድባብ በከፊል

IMG_5009 IMG_5005 IMG_4999

በጨዋታ ዙርያ ምን ተባለ?

ሁበርት ቬሉድ – የቲፒ ማዜምቢ አሰልጣኝ

‹‹ ስለ ቅዱስ ጊዮረጊስ መረጃው አለን፡፡ አምና አልጄርያ ላይ ከኤም.ሲ. ኡልማ ጋር ሲጫወቱ ተመልክተናል፡፡ ጥሩ ቡድን ነው፡፡ ኳስ አደራጅተው ለመጫወት ይሞክራሉ፡፡

‹‹ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ፊት ለመጓዝ ፍላጎት እንዳለው አውቃለሁ፡፡ እኛም እስከ መጨረሻው የመጓዝ ፍላጎት እንዳለን የታወቀ ነው፡፡ ስለዚህ ጥሩ ጨዋታ ይሆናል፡፡ በጥንቃቄ ተጫውተን ጥሩ ውጤት ይዘን ለመመለስ እንሞክራለን››

IMG_0087

በሃይሉ አሰፋ

‹‹የመጀመርያውን ጨዋታ በሜዳችን እደማድረጋችን የቤት ስራችንን መጨረስ ካለብን እዙሁ መጨረስ ይጠበቅብናል፡፡ ዋናው የቤት ስራችን ይህ ነው፡፡ አሁን ላይ ሆነን ስለ መልሱ ጨዋታ የምናስብበት ጊዜ ላይ አይደለንም፡፡››

ሮበርት ኦዶንግካራ

‹‹ወደ ሜዳ የምንገባው 11ለ11 ሆነን ነው፡፡ ጨዋታውን አቅልለን እንቻወታለን፡፡ ጥቃቀን ስህተት ላለመስራት በጥንቃቄ በመጫወት ውጤት ይዘን እንወጣለን፡፡ የሜዳችንን እና የደጋፊችንን አድቫንቴጅ ተጠቅመን እናሸንፋለን››

ዘሪሁን ሸንገታ

‹‹ ጨዋታውን ለማሸነፍ ስንዘጋጅ ቆይተናል፡፡ ተጫዋቾቹ ጋርም ጥሩ መነሳሳት አለ፡፡ ለቲፒ ማዜምቤ አክብሮት እንጂ አክብዶ የማየት ነገር በውስጣችን የለም፡፡ ጠንካራ ጎን እንዳላቸው ሁሉ ደካማ ጎንም አላቸው፡፡ እኛም የራሳችን ጠንካራ ጎን አለን፡፡

 

 

የስታድየም የመግቢያ ዋጋ

ደረጃ አንድ – 200 ብር

ደረጃ ሁለት – 50 ብር

ደረጃ ሶስት – 10 ብር

ደረጃ አራት – 5 ብር

image-2bfeab07f8b7da5ca61519d8d364c53f8edd16de69f28fef8ce58d9b29b129d3-V

ጨዋታውን የሚመሩ ዳኞች

የእለቱን ጨዋታ ስዋዚላንዳዊያን ዳኞች ይሩታል፡፡ ምቦግሴኒ ኤልየት ዋና ዳኝነቱን ሲመሩ ፔትሮስ ምዚካፊኒ ሲፊሶ ኑማሎ የጨዋታው ረዳት ዳኞች ተደርገው ተመርጠዋል፡፡ ፕሪቻርድ ንሌኮ 4ኛ ዳኛ ናቸው፡፡

ፎቶ – ከቅዱስ ጊዮርጊስ የፌስቡክ ገፅ

– – – – –

ሰላም!

በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ 1ኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታ የኢትዮጵያው ቅዱስ ጊዮርጊስ የዲ.ሪ.ኮንጎው ቲፒ ማዜምቤን ባህርዳር ላይ ያስተናግዳል፡፡
ከጨዋታው በፊት ፣ የጨዋታውን እንዲሁም የድህረ ጨዋታ መረጃዎችን በዚሁ ገፅ ላይ ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡
ከእናንተ የሚጠበቀው ገፁን በደቂቃዎች ልዩነት በመክፈት አዳዲስ መረጃ ማግኘት ነው፡፡

መልካም ቀን!

nbsp;

/strong

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *