የዋልያዎቹ የመስመር ተጫዋች ከደቡብ አፍሪካው ጨዋታ ውጪ ሆኗል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመስመር ተጫዋች መስከረም 29 እና ጥቅምት 2 ከሚደረጉት ወሳኝ ጨዋታዎች ውጪ ሆኗል።

ለ2022 የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ አፍሪካ ጋር ላለበት የምድብ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች ዝግጅቱን ባህር ዳር ላይ በመከተም እያከናወነ ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሦስት ቀናት በፊት ቁርጭምጭሚቱ ላይ ጉዳት ያጋጠመው የመስመር ተጫዋች ሽመክት ጉግሳ እረፍት ቢሰጠውም ከጉዳቱ በቶሎ አለማገገሙን ተከትሎ ከወሳኞቹ ጨዋታዎች ውጪ እንደሆነ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ተጫዋቹ በትናንትናው ዕለት ከብሔራዊ ቡድኑ በመለየት ወደ መዲናችን እንደመጣ ተጠቁሟል።

ያጋሩ