የካ ክፍለ ከተማ ምልመላ ሊያደርግ ነው

የከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ የካ ክፍለ ከተማ ስብስቡን በምልመላ ለማሟላት ጥሪ አቅርቧል።

በ2010 የውድድር ዓመት ከአንደኛ ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ ማደግ የቻለው የካ ክፍለ ከተማ በሊጉ እየተፎካከረ እስካሁን ድረስ ዘልቋል። ዘንድሮም በከፍተኛ ሊጉ ባለው ፉክክር ራሱን አጠናክሮ ለመቅረብ በማሰብ በቡድኑ ውስጥ ባሉ ክፍት ቦታዎች ላይ ተጫዋቾችን ለመመልመል ማሰቡን በፌስ ቡክ ገፁ አስታውቋል።

ምልመላው ከጥቅምት 01-05 ድረስ ጠዋት 03:00 ላይ 22 አካባቢ በሚገኘው የክለቡ የልምምድ ሜዳ (በተለምዶው 11 ሜዳ) የሚካሄድ ይሆናል። ክለቡ በተባለው ቦታ እና ሰዓት ተመልማዮች ትጥቃቸውን በማሟላት እንዲገኙም ጨምሮ አሳስቧል።

ያጋሩ