ወጣቱ አሰልጣኝ ቶማስ ግርማን ለመታደግ የድጋፍ ጥሪ ቀረበ

ለዓመታት ታዳጊዎችን በማሰልጠን የሚታወቀው ወጣቱ አሰልጣኝ ቶማስ ግርማ በጠና መታመሙን ተከትሎ የድጋፍ ጥሪ ቀርቧል።

በአዲስ አበባ በተለይ በተለምዶ 24 ሜዳ በሚባለው አካባቢ ከታዳጊ ፕሮጀክት አንስቶ የአፍሮ ፅዮን ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድን እንዲሁም የቦሌ ክፍለ ከተማ ቡድን ዋና አሰልጣኝ በመሆን የሚታወቀው ቶማስ ግርማ ከፍተኛ የሆነ የጤና መታወክ አጋጥሞት በአሳዛኝ ሁኔታ የህክምና ክትትል እየደረገለት ይገኛል።

ከህመሙ መደራረብ እና ካለው የአቅም ውስንነት አንፃር በቂ ህክምና እያገኘ አለመሆኑን በመገንዘብ ለህክምናው አስፈላጊውን ወጪ ለመሸፈን እንዲቻል ኢንስትራክተር ሰላም ዘርዓይ እና ምንያህል ተሾመ ያሉበት ኮሚቴ ተዋቅሮ ገቢ የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ ይገኛል።

የአብስራ ተስፋዬ ፣ በየነ ባንጃ እና ሌሎች ወጣት ተጫዋቾችን ለኢትዮጵያ እግርኳስ ያበረከተው አሰልጣኝ ቶማስ አሁን ካለበት ሁኔታ አገግሞ ወደሚወደው ሙያው እንዲመለስ የሁሉም ስፖርት ቤተሰብ ድጋፍ የሚፈልግ ሆኗል። በዚህም ኮሚቴው በቶማስ እህት ስም በከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት በኩል የስፖርት ቤተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪውን አቅርቧል።

ለቶማስ ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – 1000430232518

(እቴነሽ አገዘ፥ ፋሲል ግርማ እና ፀጋዬ ግርማ)