ኢትዮጵያ ከወራት በኋላ የሚጀመረው የአህጉሪቱ ትልቅ ውድድር ዋንጫ ለዕይታ ይቀርብባታል።
ላለፉት 70 ዓመታት በኢትዮጵያ ሲሰራ የቆየው ቶታል ኢነርጂስ ከአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ጋርም የረጅም ጊዜ የሥራ ግንኙነት አለው። በስሙ በተሰየመው የአህጉሪቱ ትልቁ የብሔራዊ ቡድኖች ውድድር ላይም ከስምንት ዓመታት በኋላ ተሳታፊ የሆነችው ኢትዮጵያ በድርጅቱ አማካይነት የውድድሩ አሸናፊ የሚሸለመው ዋንጫ ከሚዞርባቸው 18 ሀገራት ውስጥ አንዷ ለመሆን በቅታለች። ዋንጫው በሀገራችን ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ቶታል ኢትዮጵያም የሁነቱ ዋና አከናዋኝ ነው።
በመሆኑም የፊታችን ሰኞ የቶታል ኢነርጂስ ስታፍ እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ተወካዮች እና የተቋሙ ብራንድ አንባሳደር በተገኙበት በተቀየሙ ዋና መስሪያ ቤት በሚዘጋጅ ደማቅ ሥነስርዓት ለዕይታ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።