የዋልያዎቹ የመጀመሪያ አሰላለፍ ታውቋል

ከሰዓታት በኋላ የደቡብ አፍሪካ አቻውን የሚገጥመው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ አሠላለፍ ታውቋል።

ኳታር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በምድብ ሰባት ከደቡብ አፍሪካ፣ ዚምባቡዌ እና ጋና ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ 10 ሰዓት በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የምድብ ሦስተኛ ጨዋታውን ያደርጋል። ለዚህ ወሳኝ ጨዋታ በመጀመሪያ አሰላለፍ አሠልጣኝ ውበቱ አባተ እና ረዳቶቹ የመረጧቸውን አስራ አንድ ተጫዋቾችን ሶከር ኢትዮጰያ አግኝታለች።

ግብ ጠባቂ

ፋሲል ገብረሚካኤል

ተከላካዮች

ረመዳን የሱፍ
አስቻለው ታመነ
ያሬድ ባየህ
አስራት ቱንጆ

አማካዮች

ይሁን እንዳሻው
ሽመልስ በቀለ
ሱራፌል ዳኛቸው

አጥቂዎች

አቡበከር ናስር
ጌታነህ ከበደ
አማኑኤል ገብረሚካኤል

ያጋሩ