ደቡብ አፍሪካን የሚገጥመው የዋልያው የመጀመሪያ አሰላለፍ ታውቋል

በኤፍ ኤን ቢ ስታዲየም ከደቡብ አፍሪካ ጋር የሚጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ አሠላለፍን ሶከር ኢትዮጵያ አግኝታለች።

ኳታር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረጉ የሚገኙት ዋልያዎቹ ዛሬ ምሽት አራተኛ የምድብ ጨዋታቸውን ከደቡብ አፍሪካ ጋር ከሜዳቸው ውጪ ያደርጋሉ። ከትናንት በስትያ ጠዋት ወደ ስፍራው ያቀናው ቡድኑም ምሽት አንድ ሰዓት ለሚጀምረው ጨዋታ ዝግጅቱን ሲያደርግ የነበረ ሲሆን በጨዋታው የሚጠቀመውንም የመጀመሪያ አሰላለፍን አውቀናል።

ዋልያዎቹ ዛሬ ባደረጓቸው ሦስት ለውጦች አሰራት ቱንጆ በሱለይማን ሀሚድ ሲተኩ አማካይ ክፍል ላይ ይሁን እንዳሻው ወጥቶ አማኑኤል ዮሀንስ ተተክቷል። ሽመልስ በቀለ በመስዑድ መሀመድ የተለወጥበት ሂደትም ሌላኛው ቅያሪ ሆኗል።

ግብ ጠባቂ

ፋሲል ገብረሚካኤል

ተከላካዮች

ረመዳን የሱፍ
አስቻለው ታመነ
ያሬድ ባየህ
ሱሌይማን ሀሚድ

አማካዮች

አማኑኤል ዮሐንስ
መስዑድ መሐመድ
ሱራፌል ዳኛቸው

አጥቂዎች

አቡበከር ናስር
ጌታነህ ከበደ
አማኑኤል ገብረሚካኤል

ያጋሩ