ለሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር ዝግጅት ለተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት በሚደረገው የሴካፋ ውድድር ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።

በቅርቡ ለ2022 የኮስታሪካ የዓለም ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ማጣርያ ሁለተኛ ዙር ጨዋታውን ሩዋንዳን በማሸነፍ ወደ ተከታዩ ዙር ያለፈው ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ጥቅምት 18 በሚጀምረው የሴካፋ ውድድር ላይ የሚካፈል ሲሆን ለዚህ ውድድር እንዲረዳውም አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል። የብሔራዊ ቡድኑ አባላትም ነገ በጁፒተር ሆቴል ሪፖርት በማድረግ ዝግጅት እንደሚጀምርም ተገልፀል።

ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች

እየሩሳሌም ሎራቶ (አዳማ ከተማ)
ባንቺአየሁ ደመላሽ (ባህር ዳር ከተማ)
ምህረት ተሰማ (አርባምንጭ ከተማ)

ተከላካዮች

ነጻነት ጸጋዬ (መከላከያ)
ብርቄ አማረ (ድሬደዋ ከተማ)
ትዕግስት ኃይሌ (አርባ ምንጭ ከተማ)
የምስራች ዘውዴ (ቦሌ ክ/ከተማ)
በሻዱ ረጋሳ (አዲስ አበባ ከተማ)
መስከረም ኢሳይያስ (ኤሌክትሪክ)

አማካዮች

ገነት ኃይሉ (መከላከያ)
እጸገነት ግርማ (መከላከያ)
ኝቦኝ የን (ኤሌክትሪክ)
ዓይናለም አደራ (መከላከያ)
ማዕድን ሳህሉ (መከላከያ)
ሶፋኒት ተፈራ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ቤቲ ዘውዱ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)

አጥቂዎች

ንግስት በቀለ – (ቦሌ ክ/ከተማ)
ቱሪስት ለማ (ሀዋሳ ከተማ)
ቤተልሔም ታምሩ (ድሬዳዋ ከተማ)
ፎዚያ መሐመድ (ኢት /ን/ባንክ)
እየሩሳሌም ወንድሙ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሊዲያ ጌትነት (ባህር ዳር ከተማ)
አርያት ኦዶንግ (አዲስ አበባ ከተማ)

ያጋሩ