ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲሱ አሰልጣኝ ጉዳይ…

በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቅዱስ ጊዮርጊስ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ቡድናቸውን ያልመሩት አዲሱ አለቃ በቀጣይ ጨዋታዎች ቡድኑን ይመሩ ይሆን ?

አንጋፋው ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለዘንድሮ ዓመት የውድድር ዘመን ሰርቢያዊው አሰልጣኝ ዝላትኮ ክራምፓቲችን መቅጠሩ ይታወቃል። ቢሾፍቱ በሚገኘው የይድነቃቸው አካዳሚ ቅድመ ዝግጅቱን በዋና በአሰልጣኙ እየተመራ ሲያደርግም ቆይቷል።

ሆኖም በ15ኛው የከተማ ዋንጫ ላይ አሰልጣኝ ክራምፓቲች ቡድኑ ባደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች ላይ ቡድናቸውን እንዳልመሩ እና ምክትል አሰልጣኙ ዘሪሁን ሸንገታው ሲመራ መቆየቱ የሚታወስ ነው። ከዕይታ መራቃቸውን ተከትሎ የአሰልጣኙ በጨዋታዎቹ ላይ ያልተገኙበት ምክንያት ምን ይሆን ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም ዛሬ ማምሻውን ሶከር ኢትዮጵያ የፈረሰኞችን ቅድመ ዝግጅት ለመስራት በቢሾፍቱ ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ በተገኘችበት ወቅት አሰልጣኙ በዚህ ሳምንት ለሚጀምረው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ቡድናቸውን በልምምድ ሲያዘጋጁ ተመልክተናል።

ይህን ተከትሎ በቀጣይ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰበታ ከተማ ጋር በሚኖረው የሊጉ የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታ አንስቶ ቡድኑን በሜዳ ተገኝተው እንደሚመሩም አረጋግጠናል።