የኢትዮጵያ እግር ኳስ ደጋፊዎች ጥምረት ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለቦች ደጋፊዎች ጥምረት የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል፡፡

ከተቋቋመ ሁለት አመታትን ማስቆጠር ቢችልም ህጋዊ የሆነ መዋቅርን እስኪይዝ ጠቅላላ ጉባዔውን ለማድረግ ሳይችል የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ደጋፊዎች ማህበር ጥምረት የመጀመሪያ የሆነውን ጉባዔ በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ ማድረግ ችሏል፡፡ አቶ ኢሳይያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ተገኝተው ባደረጉት የክፈቻ ይህ ማኅበር በመቋቋሙ የፈጠረባቸው ስሜት የተለየ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ የተጠናከረ እና ሀገራዊ ስሜት ያለው ሆኖ መገኘት እንዳለበት ሲገልፁ በጠቅላላ ጉባዔውም ጠንከር ዳለ ምክረ ሀሳብን አስረድተዋል፡፡

በመቀጠል አቶ ክፍሌ ሰይፈ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሼር ካምፓኒ ሥራ አስኪያጅ ፕሪምየር ሊጉ ከዚህ ቀደም ከነበረው ይዘት በብዙ ነገሮች ተሻሽሎ የመጣ በመሆኑ ደጋፊዎች በሜዳ እና ከሜዳ ውጪ የተሻለ የአደጋገፍ ስርአትን ሊከተሉ ይገባል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ የሊግ ካምፓኒው ሥራ አስኪያጅ ስለ ደጋፊ እና ተመልካች እንዲሁም ስለ ዓለም አቀፍ ድጋፍ አሰጣጥ የተዘጋጀውን ሰነድ በፓወር ፖይንት የታገዘ ትንታኔ አቅርበዋል፡፡

ነገ ጅምሩን በሚያደርገው የ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግን በተመለከተ በጉባሤው ላይ የፀጥታ አካላት እና መሰል የሚመለከታቸው አካላት ከደጋፊዎች ጋር ስለ ውድድሩ እና አጠቃላይ ሂደት በተመለከተ ውይይት ማድረግ የቻሉ ሲሆን ከሰዓት በነበረው ፕሮግራም በሰፊው የጥምረቱ አባላት የስራ አስፈፃሚ መረጣ እና ቀጣይ አቅጣጫ ዙሪያ እስከ ምሽት ድረስ ካደረጉ በኋላ ተጠናቋል፡፡

ያጋሩ