ቅድመ ዳሰሳ | አዳማ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ

የነገውን ቀዳሚ ጨዋታ አስመልክተን እነዚህን መረጃዎች ልናቀብላችሁ ወደናል።

ዓምና በወራጅ ቀጠና ውስጥ የጨረሱት እና በክረምቱ የመለያ ውድድር ዳግመኛ ባገኙት ዕድል አብረው የተመለሱት አዳማ እና ወልቂጤ የዓመቱ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን እርስ በእርስ ያገኛሉ። ከሁለቱ መካከል አዳማ በብዙ ረገድ ተቀይሮ ሲመጣ ወልቂጤ የአምናው መልኩ በቡድኑ ውስጥ አለ።

የተመጣጠነ ፉክክር እንደሚይስመለክተን በሚጠበቀው በዚህ ጨዋታ በሁለቱም በኩል የማጥቃት ፍላጎት የሚነበብበት ፈጣን ፍልሚያ እንደሚኖር ይገመታል።

2013 ላይ በወልቂጤ ዘንድሮ ደግሞ በአዳማ ከተማ እየተጫወተ ያለው ጀማል ጣሰው መጠነኛ ህመም ስላለበት ለጨዋታው መድረሱ እርግጥ አልሆነም። በወልቂጤ በኩል ግን የተሰማ የጉዳትም ሆነ የቅጣትም ዜና የለም።

ባሳለፍነው ዓመት ከተገናኙባቸው ሁለት ጨዋታዎች አንዱን ወልቂጤ 1-0 ሲያሸንፍ ቀጣዩ ጨዋታ ያለ ግብ ተጠናቋል።

የሁለቱን ክለቦች የክረምት ወቅት ዝግጅት እና በቀጣይ የሚኖራቸውን መልክ በሰፊው ያወሳንባቸውን ፅሁፎች ከዚህ በታች ያገኛሉ።


አዳማ ከተማ

የክለቦች የውድድር ዘመን ቅድመ ዳሰሳ | አዳማ ከተማ

ወልቂጤ ከተማ

የክለቦች የውድድር ዘመን ቅድመ ዳሰሳ | ወልቂጤ ከተማ

ያጋሩ