አዳጊዎቹን ቡድኖች በሚያገናኘው ጨዋታ ዙሪያ ጥቂት ሀሳቦች አንስተናል።
በከፍተኛ ሊጉ የተደለደሉባቸውን ምድቦች በአንደኝነት በማጠናቀቅ ዳግም ወደ ፕሪምየር ሊጉ የመጡት ሁለቱ ቡድኖች በእርስ በእርስ ፍልሚያ ዓመቱን ይጀምራሉ። ከዚህ በተጨማሪ ሁለቱን ክለቦች አሰልጣኞቻቸውን ሳይቀይሩ ለውድድሩ መብቃታቸው ያመሳስላቸዋል። በስብስብ ደረጃ ግን ከአርባምንጭ ይልቅ መከላከያ ብዙ ለውጦችን አድርጓል።
በእንቅስቃሴ ረገድ የነገው ጨዋታ ጥንቃቄ አዘለ አቀራረብ ያለው አርባምንጭ ከተማ እና ኳስ መስርቶ ለመውጣት የሚሞክር መከላከያን ያስመለክተናል ተብሎ ይገመታል።
ከ2010 በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የሚገናኙት ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ ቀደም በሊጉ ለ14 ጊዜያት ተገናኝተው አራት አራት ጊዜ ተሸናንፈዋል። በቀሪው ስድስት ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። በጎል ረገድም ግንኙነቱ 21 ጎል ሲቆጠርበት በተመጣጠነ ሁኔታ አርባምንጭ 11፤ መከላከያ 10 ጎሎችን አስቆጥረዋል።
የሁለቱን ክለቦች የክረምት ወቅት ዝግጅት እና በቀጣይ የሚኖራቸውን መልክ በሰፊው ያወሳንባቸውን ፅሁፎች ከዚህ በታች ያገኛሉ።
አርባምንጭ ከተማ
https://soccerethiopia.net/football/7178011
መከላከያ
https://soccerethiopia.net/football/7171611