የዮናስ በርታ ወቅታዊ ሁኔታ

አዳማ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ላይ ጠንከር ያለ ጉዳት አስተናግዶ ወደ ሆስፒታል ያመራው ዮናስ በርታ ወቅታዊ ሁኔታ

በሊጉ የመክፈቻ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ስምንት ሰዓት ላይ አዳማ ከተማ ከ ወልቂጤ ከተማ ያደረጉትና አንድ አቻ የተጠናቀቀው ጨዋታ ላይ በ31ኛው ደቂቃ የማዕዘን ምት በሚሻማበት ወቅት የወልቂጤው ዮናስ በርታ በደረሰበት ግጭት ጉዳት ገጥሞት እንደነበር ይታወቃል። ተከላካዩ ጉዳቱ ከፍ ያለ በመሆኑም ተቀይሮ በመውጣት በቀጥታ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል መወሰዱ የሚታወስ ነው።

ዮናስ በዓይኑ አካባቢ የመስጠንቅ ጉዳት የገጠመውና ብዙ ደም የፈሰሰው ሲሆን በአምቡላንስ ሆኖ ራሱን ስቶ እንደነበርም ታውቋል። ያም ሆኖ በአዳሬ ሆስፒታል ህክምና ተደርጎለት በተሻለ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝና በአሁኑ ወቅትም ከሆስፒታል ወጥቶ ቡድኑ ወዳረፈበት ሆቴል ማምራቱ ተገልጿል። የህክምና ክትትሉንም ነገ የሚቀጥል መሆኑን የቡድን መሪው ገልፀውልናል።

ያጋሩ