የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

ኢትዮጵያ የምትሳተፍበትና በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ከያዝነው ወር ጀምሮ የሚደረገው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር በስድስት ሀገራት መካከል ይደረጋል፡፡

በአሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል የሚመራው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ለሴካፋ ከሀያ ዓመት በታች ዋንጫ ውድድር ይረዳው ዘንድ በአዲስ አበባ ቅድመ ዝግጅቱን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ይህን ውድድር በበላይነት የሚመራው ሴካፋም ውድድሩ የሚጀመርበትን እንዲሁም የውድድሩን መርሀግብር ይፋ አድርጓል፡፡

ከጥቅምት 18 -30 በዩጋንዳ በሚካሄደው ውድድር ላይ ስድስት ሀገራት በዙር ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን አዘጋጇ ዩጋንዳ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ብሩንዲ ፣ ኤርትራ ፣ ጅቡቲ እና ታንዛኒያ በውድድሩ ላይ ተካፋዮች ናቸው። ኢትዮጵያዊያን እንስቶችም በኤፍ ቲሲ ነጅሩ ስታዲየም ጥቅምት 18 በ7:30 ጅቡቲን በመግጠም ውድድራቸውን ይጀምራሉ፡፡

የኢትዮጵያ መርሐ ግብር

ጥቅምት 18 – ከጅቡቲ (7:30)
ጥቅምት 21 – ከኤርትራ (7:30)
ጥቅምት 24 – ከታንዛንያ (5:00)
ጥቅምት 27 – ከቡሩንዲ (5:00)
ጥቅምት 30 – ከዩጋንዳ (9:30)