ከፍተኛ ሊግ| ቡታጅራ ከተማ የቀድሞው አሰልጣኙን በድጋሚ ሾሟል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ተወዳዳሪ የሆነው ቡታጅራ ከተማ የቀድሞው አሰልጣኙን ዳግም ምርጫው አድርጓል፡፡

የ2013 የከፍተኛ ሊግ የምድብ ሐ ውድድሩን በአሰልጣኝ ካሊድ መሐመድ እየተመራ ዓመቱን በሰበሰበው 35 ነጥብ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቆ የነበረው ቡታጅራ ከተማ ለዘንድሮው የውድድር ዓመት ከዚህ ቀደም ክለቡን አሰልጥነው የነበሩት መሳይ በየነን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ በማድረግ በድጋሚ ሾሟል፡፡

በቀድሞው አጠራሩ ጅማ ከነማ ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፣ የኢትዮጵያ መድን ረዳት አሰልጣኝ ፣ የነቀምት እና ዱከም ከተማ እንዲሁም የፌድራል ፓሊስ አሰልጣኝ ሆነው የሰሩት አሰልጣኝ መሳይ ከዚህ ቀደም ማለትም 2007 እና 2008 ቡታጅራ ከተማን በዋና አሰልጣኝነት መርተው የነበሩ ሲሆን ከአምስት ዓመታት በኋላ ዳግም የክለቡ ተመራጭ አሰልጣኝ በመሆን በኃላፊነት መሾማቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ የደረሳት መረጃ ያመላክታል፡፡

ያጋሩ