ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ቅዱስ ጊዮርጊስ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በ2014 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪ መሆኑን ያረጋገጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ አስራ አንድ አዳዲስ ተጫዋቾች ሲያስፈርም የአስራ ሁለት ነባሮችን ውልም አድሷል፡፡

በአሰልጣኝ ራውዳ አሊ እየተመራ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ውድድር ላይ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ሲሳተፍ ቆይቶ ባህር ዳር ከተማ እና ቦሌ ክፍለ ከተማን ተከትሎ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ በማጠናቀቅ ዓመቱን የፈፀመው ቅዱስ ጊዮርጊስ ምንም እንኳን በ2013 ይዞ ያጠናቀቀበት ደረጃ ወደ አንደኛ ዲቪዚዮን የሚያሳድገው ውጤት ያልነበረ ቢሆንም በቅርቡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በፕሪምየር ሊጉ የተሳታፊ ክለቦች ቁጥርን ለማሳደግ በወሰነው መሰረት የፈረሰኞቹ እንስቶች በፕሪምየር ሊጉ አንደኛ ዲቪዚዮን መሳተፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ይህንንም ተከትሎ ክለቡ ጠንካራ እና ተፎካካሪ ለመሆን በማሰብ ወደ ዝውውር ገበያው ጎራ በማለት ከተለያዩ ክለቦች ቡድኑ አስራ አንድ አዳዲስ ተጫዋቾች ማስፈረም ሲችል የአስራ ሁለት ነባር ተጫዋቾችን ኮንትራት በአንፃሩ አድሷል፡፡

ዓይናለም ሽታ (ከድሬደዋ ከተማ ግብ ጠባቂ)፣ ፅሆን ተፈራ (ለገጣፎ ለገዳዲ ግብ ጠባቂ)፣ በረከት ዘመድኩን (ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ ግብ ጠባቂ)፣ እመቤት ስማቸው (ከንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ተከላካይ)፣ ሰላም በቃኸኝ (ከልደታ ክ/ከተማ ተከላካይ)፣ ሊዲያ እንዲሪስ (ከለገጣፎ ለገዳዲ ተከላካይ)፣ እቴነሽ ደስታ (አራዳ ክ/ከተማ ተከላካይ)፣ አዲስ ዘውገ (ከጥሩነሽ አካዳሚ አማካይ)፣ ብዙአየሁ ፀጋዬ (ከንፋስ ስልክ ክ/ከተማ አማካይ)፣ ቤቴልሄም መንተሉ (ከቦሌ ክ/ከተማ አጥቂ)፣ እመቤት ፋንታሁን (ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ አጥቂ) ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲስ ፈራሚ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡

ከአዳዲስ ተጫዋቾች በተጨማሪ ክለቡ የነባር አስራ ሁለት ተጫዋቾችን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል፡፡ ሶፋኒት ተፈራ (አማካይ)፣ ንግስት አስረስ (ተከላካይ)፣ ገብሬኤላ አበበ (አማካይ)፣ ፍቅርአዲስ ገዛኸኝ (አጥቂ)፣ እየሩሳሌም ወንድሙ (አጥቂ)፣ ዳግማዊት ሰለሞን (አጥቂ)፣ ቤተልሄም ስለሺ (ተከላካይ)፣ ዓይናለም ዓለማየሁ (አጥቂ)፣ መስከረም መኮንን (አማካይ)፣ ቤቴልሄም አሰፋ (አማካይ)፣ ሰናይት ሸጎ (ተከላካይ)፣ ሰላም ፍቃዱ (አጥቂ) ከክለቡ ጋር በአንደኛ ዲቪዚዮኑ የምናያቸው ይሆናል፡፡

በቅርቡ ወደ ዝግጅት ለመግባት በሂደት ላይ የሚገኘው ክለቡ በቀጣዮቹ ቀናትም የአሰልጣኝ ራውዳ አሊን ውል ለማራዘም በሒደት ላይ እንደሆነም ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡