ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | ቦሌ ክ/ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ሲሾም ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾችን አስፈርሟል

ከኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ወደ አንደኛው ዲቪዚዮን ያደገው ቦሌ ክፍለ ከተማ ለ2014 የውድድር ዘመን አዲስ አሰልጣኝ ሲሾም አስራ ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዲቪዮን ሲወዳደር ቆይቶ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ባህር ዳር ከተማን በመከተል ሁለተኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ማደጉን አረጋግጦ የነበረው ቦሌ ክፍለ ከተማ ለዘንድሮው የውድድር ዓመት ተጠናክሮ በሊጉ ለመቅረብ ይረዳው ዘንድ በወጣቶች ስፖርት አካዳሚ በአሰልጣኝነት ሲያገለግል የነበረው አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻን በዋና አሰልጣኝነት ያመጣ ሲሆን ቡድኑም የነባር ተጫዋቾችን ውል ሲያድስ አስራ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችንም አስፈርሟል፡፡

አዳዲስ ፈራሚዎች ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የምስራች ሞገስ (ተከላካይ)፣ ንግስት በቀለ (አጥቂ)፣ ሜላት አሊሙዝ (አማካይ)፣ ትዕግስት ሙሉዓለም (አማካይ)፣ ሊንጎ ኦማን (ግብ ጠባቂ)፣ ትርሲት ወንድወሰን (ተከላካይ)፣ ሲፈን ተስፋዬ (አማካይ)፣ቃልኪዳን ንቅበሸዋ (ተከላካይ) እና ብዙነሽ እሸቱ ተከላካይ ከአሰልጣኝ ቻለው ጋር ክለቡን የተቀላቀሉ ናቸው። ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ በአንፃሩ ሂሩት ተስፋዬ (ተከላካይ)፣ ጤናዬ ለታሞ (አጥቂ)፣ ሂሩት ብርሀኑ (ተከላካይ) ስንታየሁ ኢርኮ (ከለገጣፎ ለገዳዲ አጥቂ)፣ ትብቃ ፈንቴ (ግብ ጠባቂ ከባህርዳር ከነማ) ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲስ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ከአዲሶቹ ባሻገር ውል ያደሱ ስድስት የክለቡ ተጫዋቾች መዓዛ አብደላ (አማካይ)፣ ምስጋና ግርማ (አማካይ)፣ ንጋት ጌታቸው (ተከላካይ)፣ ምርጥነሽ ዮሐንስ (አጥቂ)፣ አስቴር ደግአረገ (አጥቂ) እና ሜላት ጌታቸው (አጥቂ) ናቸው.

ያጋሩ