ሴቶች ፕሪምየር ሊግ | አቃቂ ቃሊቲ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ተወዳዳሪ የሆነው አቃቂ ቃሊቲ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል፡፡

የ2013 የኢትዮጵያ ሴቶችን ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ውድድርን በአሰልጣኝ ብዙዓየው ዋዳ መሪነት ቢጀምርም በስተመጨረሻም ክለቡ ባስመዘገበው ውጤት መነሻነት አሰልጣኙን በማሰናበት በረዳት አሰልጣኙ ጥበቡ የመጨረሻ ሦስት ጨዋታዎች ከተመራ በኋላ ወደ ሁለተኛ ዲቪዚዮን ለመውረድ መገደዱ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2014 የውድድር ዘመን በአንደኛ ሊጉ ያሉ ክለቦችን ቁጥር ለመጨመር በማሰቡ ወርዶ የነበረው አቃቂ ቃሊቲም በፕሪምየር ሊጉ እንዲቀጥል የሚል ውሳኔን በማሳለፉ በፕሪምየር ሊጉ በአዲስ አሰልጣኝ ለመቅረብ በተጠናቀቀው የውድድር አመት ማስታወቂያ አውጥቶ አሰልጣኝ ብዙዓየው ዋዳን ተከትለው ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመሆን ማጠናቀቅ ችለው የነበሩት አሰልጣኝ አሰልጣኝ ዮናስ ወርቁን እንዲሁም የኔነህን ጠርቶ የቃል ፈተና ከፈተነ በኋላ በመጨረሻም ክለቡ ዮናስ ወርቁን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ መርጦታል፡፡

አሰልጣኝ ዮናስ በተለያዩ ወቅቶች በአዲስ አበባ የተለያዩ ቡድኖችን እነዲሁም በቅድስት ማርያም ዩኒቨርሲቲ እና እስካለፈው ዓመት አጋማሽ ድረስ በልደታ ክፍለ ከተማ አሰልጣኝነት ከሰነበተ በኋላ አዲሱ የአቃቂ ቃሊቲ አሰልጣኝ ተደርጎ ተሹሟል፡፡