የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች እንዲህ ተጠናቅረዋል።
በመጀመሪያው የሊጉ መርሐ-ግብር በድሬዳዋ ከተማ የተረቱት ወላይታ ድቻዎች የመጀመሪያ ድላቸውን ለማግኘት አንድ ለውጥ ብቻ አድርገው ዛሬ ወደ ሜዳ ይገባሉ። በዚህም አሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ቃልኪዳን ዘላለምን አሳርፈው ያሬድ ዳዊትን ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ አምጥተዋል።
በመቀመጫ ከተማቸው ውድድር እያደረጉ የሚገኙት ሀዋሳ ከተማዎች ደግሞ ጅማ ላይ ድል ሲያገኙ ከተጠቀሙት አሰላለፍ ሁለት ለውጥ አድርገዋል። በዚህም መድሃኔ ብርሃኔ እና ዳዊት ታደሠ ዳንኤል ደርቤ እና በቃሉ ገነነን ተክተው ወደ ሜዳ ገብተዋል።
ከጨዋታው መጀመር በፊት ፀጋዬ ኪዳነማርያም በድሬው ጨዋታ የተሳሳቱትን ለመድገም እንዳልመጡ ጠቅሰው ተጋጣሚያቸው ስድስት ነጥብ ለማግኘት ስለሚገባ ትኩረት ሰጥተው ድል የሚያገኙበትን አጨዋወት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
አሠልጣኝ ዘርዓይ በበኩላቸው ወላይታ ድቻ ጠንካራ ቡድን ነው ካሉ በኋላ የተወሰኑ ተጫዋቾችን ለውጠው ቢገቡም ለማሸነፍ በማጥቃት ላይ ያተኮረ አጨዋወት እንደሚጫወቱ ተናግረዋል።
ሽንፈት እና ድል በመጀመሪያው ሳምንት አስመዝግበው ለዚህኛው ጨዋታ የቀረቡት ድቻ እና ሀዋሳ የሚያደርጉትን ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ኃይለእየሱስ ባዘዘው የሚመሩት ይሆናል።
የሁለቱ ቡድኖች አሰላለፍ ደግሞ እንደሚከተለው ተቀምጧል።
ወላይታ ድቻ
99 ጽዮን መርዕድ
4 በረከት ወልደዮሐንስ
26 አንተነህ ጉግሳ
12 ደጉ ደበበ
16 አናጋው ባደግ
20 ሀብታሙ ንጉሤ
25 ንጋቱ ገብረስላሴ
8 እድሪስ ሰዒድ
9 ያሬድ ዳዊት
11 ምንይሉ ወንድሙ
10 ስንታየሁ መንግሥቱ
ሀዋሳ ከተማ
31 ዳግም ተፈራ
16 ወንድሜነህ ማዕረግ
26 ላውረንስ ላርቴ
6 አዲስዓለም ተስፋዬ
14 መድሃኔ ብርሃኔ
18 ዳዊት ታደሰ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
13 አብዱልባሲጥ ከማል
21 ኤፍሬም አሻሞ
10 መስፍን ታፈሰ
17 ብሩክ በየነ