አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | አዲስ አበባ ከ አርባምንጭ ከተማ

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀምረውን ጨዋታ የተመለከቱ የመጨረሻ መረጃዎችን እነሆ !

በሽንፈት ውድድሩን የጀመሩት ሁለቱ ቡድኖች በርካታ ለውጦችን በማድረግ ወደ ሜዳ ይገባሉ። አዲስ አበባ ከተማዎች በኋላ መስመራቸው ላይ ባደረጓቸው ለውጦች ግብ ጠባቂው ወንድወሰን ገረመውን በዳንኤል ተሾመ ሲተኩ በተከላካይ መስመራቸው ላይ ሳሙኤል አስፈሪ ፣ ሮቤል ግርማ እና ልመንህ ታደሰ የአሰጋኸኝ ጴጥሮስ ፣ ዘሪሁን አንሼቦ እና ሳሙኤል ተስፋዬን ቦታ ተክተዋል። በሌላኛው የቡድኑ ለውጥም ብዙአየሁ ሰይፉ በእንዳለ ከበደ ቦታ ይጀምራል።

በአርባምንጭም በኩል አምስት ለውጦች ሲደረጉ አሸናፊ ፊዳ ፣ ተካልኝ ደጀኔ ከኋላ አንዷለም አስናቀ ፣ በላይ ገዛኸኝ እና ራምኬል ሎክ በመሀል እና በፊት መስመር ዛሬ የምናያቸው ተጫዋቾች ናቸው። አንድነት አዳነ ፣ መላኩ ኤሊያስ ፣ አቡበከር ሸሚል ፣ ጉዳት የገጠመው ሱራፌል ዳንኤል እና አሸናፊ ተገኝ ደግሞ በምትካቸው የሚያርፉ ተጫዋቾች ናቸው።

ከጨዋታ በፊት በተሰጡ አስተያየቶች አሰልጣኝ ኢስማኤል አቡበከር በከፍተኛ ሊጉ ተጋጣሚዎቹ አንደኛ ሆነው መጨረሳቸው እንደሚያመሳስላቸው አንስተው ለማሸነፍ ብርቱ ፉክክር እንደሚኖር በመጠቆም ለማጥቃት እንደሚጫወቱ ተናግረዋል። የአርባምንጩ አቻቸው አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በበኩላቸው የመጀመሪያ ጨዋታቸው ለሁለቱም አለመሳካቱን አስታውሰው ለማሸነፍ እንድሚጫወቱ ተናግረዋል።

ፌደራል ዳኛ ሚካኤል ጣዕመ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት ተመድበዋል።

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያ አሰላለፋቸው ውስጥ ቀጣዮቹን ተጫዋቾች አካትተዋል።

አዲስ አበባ ከተማ

30 ዳንኤል ተሾመ
14 ልመንህ ታደሰ
2 ሳሙኤል አስፈሪ
22 ኢያሱ ለገሰ
19 ሮቤል ግርማ
18 ሙለቀን አዲሱ
24 ዋለልኝ ገብሬ
16 ያሬድ ሀሰን
8 ብዙአየሁ ሰይፉ
10 ፍፁም ጥላሁን
12 ቢኒያም ጌታቸው

አርባምንጭ ከተማ

1 ሳምሶን አሰፋ
14 ወርቅይታደል አበበ
4 አሸናፊ ፊዳ
25 ማርቲን ኦኮሮ
2 ተካልኝ ደጀኔ
21 አንዷለም አስናቀ
8 አብነት ተሾመ
17 አሸናፊ ኤሊያስ
9 በላይ ገዛኸኝ
10 ራምኬል ሎክ
22 ፀጋዬ አበራ