ሉሲዎቹ ለወሳኙ ጨዋታ የሚጠቀሙት አሰላለፍ ታውቋል

ዛሬ 10 ሰዓት ከዩጋንዳ አቻው ጋር ወሳኝ ጨዋታ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ አሰላለፍ ታውቋል።

ሞሮኮ ለምታስተናግደው የ2022 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታ ከዩጋንዳ ጋር መደልደሉ ይታወቃል። ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታውንም ከሜዳው ውጪ በሴንት ሜሪ ስታዲየም አከናውኖ 2-0 በሆነ ውጤት የተሸነፈ ሲሆን የመልስ ጨዋታውን ደግሞ 10 ሰዓት በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ያደርጋል።

የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው እና ረዳቶቹ ለወሳኙ ጨዋታ ወደ ሜዳ የሚያስገቧቸው ተጫዋቾችም ታውቀዋል። በዚህም ከመጀመሪያው ጨዋታ በተከላካይ ክፍሉ ላይ የነበሩት መስከረም ካንኮ እና እፀገነት ብዙነህ በትትታ ኃይለሚካኤል እና ብዙዓየሁ ታደሠ ሲተኩ አማካይ መስመር ላይም ብርቱካን ገብረክርስቶስ በህይወት ደንጊሶ ተለውጣ ወደ ሜዳ እንደምትገባ ታውቋል።

የቡድኑ አሠላለፍ የሚከተለው ነው

ግብ ጠባቂ

ታሪኳ በርገና

ተከላካዮች

ናርዶስ ጌትነት
ሀሳቤ ሙሳ
ትዝታ ኃይለሚካኤል
ብዙዓየሁ ታደሠ

አማካዮች

እመቤት አዲሱ
ብርቱካን ገብረክርስቶስ
አረጋሽ ካልሳ

አጥቂዎች

ሴናፍ ዋቁማ
ሎዛ አበራ (አ)
መዲና ዐወል