አዲስ አበባ ከተማ አሰልጣኙን አግዷል

በአሰልጣኙ እና በቡድን መሪው መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት ጉዳዩን እየተመለከተው የሚገኘው ክለቡ በአሰልጣኙ ላይ የዕግድ ውሳኔ አሳልፏል።

የአዲስ አበባ እግርኳሰ ክለብ ከሜዳ ላይ ውጤት ማጣቱ ባሻገር ከሜዳ ውጭ በተለያዩ ውዝግቦች ከወዲሁ እየታመሰ ይገኛል። በአሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር እና በቡድን መሪው ሲሳይ ተረፈ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እና ሰጣ ገባ ለመዳኘት የክለቡ ዲሲፒሊን ኮሚቴ ሁለቱም አካላት ያለውን ሁኔታ እንዲያስረዱ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ዛሬ ረፋድ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ አድርጓል።

በሁለቱም አካላት ሦስት ገፅ በያዘው የከሳሽ እና የምላሽ ሰጪ ደብዳቤ ላይ ሰፋ ያለ ሁኔታውን የሚያስረዳ ማብራሪያ ያስቀመጡ ሲሆን የቡድን መሪው ሲሳይ “ከጨዋታው አስቀድመው በፊት ጥርሴ ላይ በቦክስ በመማታት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውብኛል” ሲሉ በአንፃሩ አሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር “ስብናዬን በሚነካ መልኩ አልሻባብ እና አልቃይዳ በሚል ቡድን ተሰድቤያለሁ” በማለት ገልፀዋል። (የሁለቱም ቅሬታ ከስር በደብዳቤ ተቀምጧል)

የክለቡ የዲሲፒሊን ኮሚቴ የሁለቱንም ደብዳቤ የተቀበለ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ለክለቡ ቦርድ አቅርቦ ውሳኔ የሚሰጥ ሲሆን እስከዛው ግን አሰልጣኝ እስማኤልን አቡበከርን በጊዜያዊነት ማገዱን በደብዳቤ አሳውቋል።


የእግድ ደብዳቤ 👇


የአሰልጣኝ እስማኤል የምላሽ ደብዳቤ👇


የቡድን መሪው አቶ ሲሳይ የምላሽ ደብዳቤ👇