አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ሀዋሳ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና

የሦስተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች የመክፈቻ መርሐ-ግብርን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች እንዲህ ተሰናድተዋል።

በሊጉን የመክፈቻ ጨዋታ ጅማን ካሸነፉ በኋላ በሁለተኛው ሳምንት በወላይታ ድቻ የተረቱት ባለሜዳዎቹ ሀዋሳ ከተማዎች ሦስት ነጥብ ካስረከቡበተ ፍልሚያ አራት ተጫዋቾችን ለውጠዋል። በዚህም ግብ ጠባቂው ዳግም ተፈራን ጨንሮ አዲስ ዓለም ተስፋዬ፣ መድሃኔ ብርሃኔ እና ዳዊት ታደሠ ሲያርፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ክለቡን ለማገልገል የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ የገባው መሐመድ ሙንታሪ፣ ዳንኤል ደርቤ፣ ዮሐንስ ሴጌቦ እና በቃሉ ገነነ ወደ ሜዳ ገብተዋል። ከጨዋታው መጀመር በፊት የቀድሞ ክለባቸውን የሚገጥሙት አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ በደርቢው ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚታይበት ገምተው ቡድናቸው ከጨዋታ ጨዋታ እድገት እያሳየ እንደሆነ አመላክተዋል።

ድሬዳዋ ከተማን በሁለተኛ ሳምንት አሸንፈው ለዛሬው ጨዋታ የቀረቡት ሲዳማ ቡናዎች ደግሞ ተከላካያቸው ጊት ጋትጉትን በተስፋዬ በቀለ ብቻ ተክተው ጨዋታውን ለማድረግ ሜዳ ደርሰዋል። አሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌም በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው ሀዋሳ ከተማ ጥሩ ቡድን መሆኑን ገልፀው የሚገባቸውን ክብር ሰጥተው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ አመላክተዋል።

ሀዋሳ ከተማ

77 መሐመድ ሙንታሪ
7 ዳንኤል ደርቤ
26 ላውረንስ ላርቴ
5 ፀጋሰው ድማሙ
13 አቡዱልባሲጥ ከማል
19 ዮሐንስ ሴጌቦ
8 በቃሉ ገነነ
29 ወንድማገኝ ኃይሉ
21 ኤፍሬም አሻሞ
17 ብሩክ በየነ
10 መስፍን ታፈሰ

ሲዳማ ቡና

30 ተክለማሪያም ሻንቆ
3 አማኑኤል እንዳለ
4 ተስፋዬ በቀለ
5 ያኩቡ መሀመድ
21 ሰለሞን ሀብቴ
16 ብርሀኑ አሻሞ
15 ቴዎድሮስ ታፈሰ
7 ፍሬው ሰለሞን
14 ብሩክ ሙሉጌታ
25 ፍራንሲስ ካሀታ
11 ይገዙ ቦጋለ