ከደቂቃዎች በኋላ የሚደረገው ጨዋታ መጀመር አስቀድሞ ቀጣዮቹን መረጃዎች እንድትካፈሉ ጋብዘናል።
በሁለተኛ ሳምንት ከተጫወቱበት የመጀመሪያ አሰላለፍ አብዲሳ ጀማልን ብቻ በአቡበከር ወንድሙ ተክተው ወደ ሜዳ የገቡት አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ስህተቶቻቸውን ከጨዋታ ጨዋታ ለማረም እየሰሩ እንደሆነ እና ቡድናቸውን ለማሻሻል እየጣሩ እንደሆነ በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው ጠቁመዋል።
በተቃራኒው አንድም ለውጥ ሳያደርጉ ወደ ሜዳ የገቡት የወላይታ ድቻው አሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም በበኩላቸው ሊጉ ለእረፍት ከመቋረጡ በፊት የተገኘውን ጨዋታ አሸንፈው ቡድኑ ላይ ያለውን ስነ ልቦና ለማሰደግ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ አመላክተዋል።
ይህንን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የሚመሩት ፌደራል ዳኛ ዮናስ ካስሣሁን ናቸው።
ሁለቱ ቡድኖች በዛሬው ጨዋታ ወደ ሜዳ ይዘዉት የሚገቡት አሰላለፍ እንደሚከተለው ነው።
አዳማ ከተማ
1 ሴኮባ ካማራ
4 ሚሊዮን ሠለሞን
13 አሚን ነስሩ
80 ቶማስ ስምረቱ
7 ደስታ ዮሐንስ
6 ዮሴፍ ዮሐንስ
14 ኤሊያስ ማሞ
8 አማኑኤል ጎበና
27 አቡበከር ወንድሙ
9 አሜ መሐመድ
12 ዳዋ ሁቴሳ
ወላይታ ድቻ
99 ፅዮን መርዕድ
26 አንተነህ ጉግሳ
12 ደጉ ደበበ
4 በረከት ወልደዮሐንስ
9 ያሬድ ዳዊት
8 እድሪስ ሰዒድ
25 ንጋቱ ገብረስላሤ
20 ሀብታሙ ንጉሴ
16 አናጋው ባደግ
11 ምንይሉ ወንድሙ
10 ስንታየሁ መንግስቱ