የዕለቱን የመክፈቻ ጨዋታ የተመለከቱ መረጃዎች እንደሚከተለው ተሰናድተዋል።
ሀዲያ ሆሳዕናን በኦሴ ማውሊ የመጨረሻ ደቂቃ ጎል አሸንፈው ለዚህኛው ጨዋታ የቀረቡት ባህርዳሮች አንድ ለውጥ ብቻ አድርገዋል። በዚህም አምበላቸው ፍቅረሚካኤል ዓለሙን በአብዱልከሪን ንኪማ ብቻ ተክተዋል። የቡድኑ አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱም በድህረ ጨዋታ አስተያየታቸው ለሁሉም ቡድኖች በሚሰጡት እኩል ግምት ጨዋታውን እንደሚቀርቡ አመላክተው በአሰላለፋቸው ላይ ጉዳት ካለበት ፍቅረሚካኤል ውጪ ለውጥ እንዳላደረጉ ተናግረዋል።
በተቃራኒው በሁለተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ቡድናቸው በፋሲል ከነማ አንድ ለምንም የተሸነፈባቸው አሠልጣኝ ጻውሎስ ጌታቸው ደግሞ ከሱፐር ስፖርት ጋር ባደረጉት ቆይታ አጥቅተው ሜዳ ላይ እንደሚጫወቱ አውስተው ጠንካራ ስብስብ እንዳላቸው ጠቁመዋል። አሠልጣኙም ሦስት ነጥብ ካስረከቡበት ጨዋታ ሁለት ለውጦችን አድርገው ወደ ሜዳ ገብተዋል። በዚህም ያሬድ ታደሰ እና አበባው ቡጣቆን በረመዳን የሱፍ እና አህመድ ሁሴን ለውጠዋል።
ይህንን ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የሚመሩት ፌደራል ዳኛ ማኑኔ ወልደፃዲቅ ናቸው።
ሁለቱ ቡድኖች በዛሬው ጨዋታ ወደ ሜዳ ይዘዉት የሚገቡት አሰላለፍ እንደሚከተለው ነው።
ባህር ዳር ከተማ
44 ፋሲል ገብረሚካኤል
13 አህመድ ረሺድ
6 መናፍ ዐወል
15 ሰለሞን ወዴሳ
2 ፈቱዲን ጀማል
7 ግርማ ዲሳሳ
27 አብዱልከሪን ንኪማ
25 አለልኝ አዘነ
10 ፉዓድ ፈረጃ
14 ፍፁም ዓለሙ
77 ኦሴ ማዉሊ
ወልቂጤ ከተማ
1 ሲልቪያን ህቦሆ
12 ተስፋዬ ነጋሽ
19 ዳግም ንጉሴ
24 ውሀብ አዳምስ
3 ረመዳን የሱፍ
21 ሀብታሙ ሸዋለም
8 በኃይሉ ተሻገር
14 አብዱልከሪም ወርቁ
7 ጫላ ተሺታ
10 አህመድ ሁሴን
9 ጌታነህ ከበደ