አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ፋሲል ከነማ ከጅማ አባጅፋር

ከደቂቃዎች በኋላ የሚጀመረውን ጨዋታ የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃ እንደሚከተለው ቀርበዋል።

ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎችን አሸንፈው ለዛሬው ፍልሚያ የቀረቡት ዐፄዎቹ ሦስት ነጥብ ከሸመቱበት የወልቂጤው ጨዋታ ሁለት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም ጉዳት ያስተናገዱት ሱራፌል ዳኛቸው እና ሰዒድ ሀሰን በአምሳሉ ጥላሁን እና አብዱልከሪም መሐመድ ተለውጠዋል።

እስካሁን አንድም ነጥብ ያላስመዘገቡት ጅማ አባጅፋሮች በበኩላቸው በአዳማ ከተማ ከተሸነፉበት የመጀመሪያ አሰላለፍ ላይ አራት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም በግብ ብረቶቹ መሐከል የሚቆመው ታምራት ዳኜን በዮሐንስ በዛብህ፣ አሳህሪ አልማዲን በማላ፣ ሱራፌል አወልን በአስናቀ ሞገስ እንዲሁም እዮብ አለማየሁን በሽመልስ ተገኝ ተተክተዋል።

ጨዋታው በአሸብር ሰቦቃ ዋና ዳኝነት ሲካሄድ ዳንኤል ጥበቡ እና ሙስጠፋ መኪ ረዳቶች ባህሩ ተካ ደግሞ አራተኛ ዳኛ ሆነው ተመድበዋል።

ሁለቱ ቡድኖች በዛሬው ጨዋታ ወደ ሜዳ ይዘዉት የሚገቡት የመጀመሪያ አሰላለፍም የሚከተከው ነው።

ፋሲል ከነማ

1 ሚኬል ሳማኬ
2 አብዱልከሪም መሐመድ
16 ያሬድ ባየህ
15 አስቻለው ታመነ
5 ከድር ኩሊባሊ
21 አምሳሉ ጥላሁን
17 በዛብህ መለዮ
14 ሀብታሙ ተከስተ
19 ሽመክት ጉግሳ
7 በረከት ደስታ
9 ፍቃዱ ዓለሙ

ጅማ አባጅፋር

1 ዮሐንስ በዛብህ
20 በላይ አባይነህ
18 ያብስራ ሙሉጌታ
19 ሽመልስ ተገኝ
9 ዱላ ሙላቱ
12 ሮጀር ማላ
5 ተስፋዬ መላኩ
33 አስናቀ ሞገስ
24 መሐመድ ኑርናስር
3 መስዑድ መሐመድ
17 ዳዊት ፍቃዱ

ያጋሩ