አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል

ለዓለም ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ሁለት ጨዋታዎችን ለማድረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።

በኳታር አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታውን ከደቡብ አፍሪካ፣ ዚምባቡዌ እና ጋና ጋር እያደረገ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምንም እንኳ ከምድብ ማለፍ ባይችልም ቀሪ ጨዋታዎችን ህዳር 2 እና 5 ከጋና እና ዚምባቡዌ ጋር ያደርጋል። ለእነዚህ ሁለት ጨዋታዎችም አሠልጣኝ ውበቱ አባተ ከደቂቃዎች በፊት ለ26 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾች

ግብ ጠባቂዎች

ተክለማርያም ሻንቆ (ሲዳማ ቡና)፣ ፋሲል ገብረሚካኤል (ባህር ዳር ከተማ)፣ ፍሬው ጌታሁን (ድሬዳዋ ከተማ)

ተከላካዮች

ረመዳን የሱፍ (ወልቂጤ ከተማ ደስታ ዮሐንስ (አዳማ ከተማ) አሥራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና) አህመድ ረሽድ (ባሕር ዳር ከተማ) ያሬድ ባየህ (ፋሲል ከነማ) አስቻለው ታመነ (ፋሲል ከነማ) ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) መናፍ ዐወል (ባሕር ዳር ከተማ)

አማካዮች

አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና) ሀብታሙ ተከስተ (ፋሲል ከነማ) ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ) መስዑድ መሐመድ (ጅማ አባ ጅፋር) ሽመልስ በቀለ (ኤል ጎውና/ግብፅ) ሀይደር ሸረፋ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፍሬው ሰለሞን (ሲዳማ ቡና) በዛብህ መለዮ (ፋሲል ከነማ)

አጥቂዎች

አቡበከር ናስር (ኢትዮጵያ ቡና) ጌታነህ ከበደ (ወልቂጤ ከተማ) አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ) አማኑኤል ገ/ሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ) መስፍን ታፈሰ (ሀዋሳ ከተማ)  ዳዋ ሆቴሳ (አዳማ ከተማ) ሽመክት ጉግሳ (ፋሲል ከነማ)

 

ከላይ የተዘረዘሩት ተጫዋቾች ሊጉ ሰኞ ከተቋረጠ በኋላ በማግስቱ ጥቅምት 23 ከቀኑ 7:00 ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል ሪፖርት በማድረግ ዝግጅታቸውን አዲስ አበባ ላይ እንደሚጀምሩም ተመላክቷል።

ያጋሩ