አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | ኢትዮጵያ ቡና ከ ሰበታ ከተማ

የሦስተኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታን የተመለከቱ ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚከተለው ተሰናስለዋል።

በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ ከሲዳማ ቡና ጋር አቻ በመለያየታቸው አንድ ነጥብ ያገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች በሸገር ደርቢ አራት ለአንድ ከተረቱበት የመጀመሪያ አሰላለፍ አንድም ለውጥ ሳያደርጉ ወደ ሜዳ ገብተዋል።

እንደ ኢትዮጵያ ቡና ሁሉ በመጀመሪያው ጨዋታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ነጥብ ተጋርተው ሁለተኛውን ጨዋታ የተረቱት ሰበታዎች ሦስት ለውጦችን በመጀመሪያ አሰላለፋቸው ውስጥ አድርገዋል። በዚህም ቢያድግልኝ ኤሊያስ፣ አብዱልሀቪዝ ቶፊቅ እና ፍፁም ገብረማሪያምን በወልደአማኑኤል ጌቱ፣ ዘካሪያስ ፍቅሬ እና በበሃይሉ ግርማ ለውጠዋል።

የኢትዮጵያ ቡናው አሠልጣኝ ካሣዬ አራጌ ከጨዋታው መጀመር በፊት በሁለቱ ጨዋታዎች ነጥብ መጣላቸው ተጫዋቾቹ ላይ ተፅዕኖ እንዳለው አውስተው ጫናውን ለማስወገድ እንደጣሩ እና የሚፈልጉትን አጨዋወት ተግባራዊ አድርገው ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ተናግረዋል። የሰበታ ከተማው አሠልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ደግሞ በሁለቱ ጨዋታዎች ውጤት ባያገኙም ገና ሊጉ እየጀመረ ስለሆነ ያን ያህል ጫና እንደሌለው ተናግረው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያላቸውን ጥሩ ሪከርድ እንደሚያስቀጥሉ አመላክተዋል።

እኩል አንድ ነጥብ ይዘው በግብ እዳ ተበላልጠው 13ኛ እና 12ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ቡድኖች የሚያረጉትን ይህንን ጨዋታም ፌደራል ዳኛ ዳንኤል ግርማይ በመሀል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

ሁለቱ ቡድኖች በዛሬው ጨዋታ ወደ ሜዳ ይዘዉት የሚገቡት የመጀመሪያ አሰላለፍም የሚከተከው ነው።

ኢትዮጵያ ቡና

99 አቤል ማሞ
18 ኃይሌ ገብረትንሳይ
14 ቴዎድሮስ በቀለ
2 አበበ ጥላሁን
11 አሥራት ቱንጆ
8 አማኑኤል ዮሐንስ
5 ታፈሰ ሰለሞን
25 ሮቤል ተክለሚካኤል
10 አቡበከር ናስር
9 አቤል እንዳለ
16 እንዳለ ደባልቄ

ሰበታ ከተማ

30 ለዓለም ብርሀኑ
5 ጌቱ ኃይለማሪያም
15 በረከት ሳሙኤል
6 ወልደአማኑኤል ጌቱ
23 ኃይለሚካኤል አደፍርስ
21 በሃይሉ ግርማ
27 ክሪዚስቶም ንታንቢ
7 ዱሬሳ ሹቢሳ
9 ሳሙኤል ሳሊሶ
10 ዘካሪያስ ፍቅሬ
20 ጁኒያስ ናንጄቦ