የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ቡና 0-0 ሰበታ ከተማ

ያለ ግብ በአቻ ውጤት ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

ካሣዬ አራጌ – ኢትዮጵያ ቡና

ስለጨዋታው

“ጥሩ ነው። ተጋጣሚ ጎል አካባቢ ስንደርስ ትንሽ የመቸኮል ነገር ቶሎ የመጨረሻውን ሰው የመፈለግ ነገር ነበር ፤ በተረፈ ግን ጥሩ ነበር።”

በሁለተኛው አጋማሽ የተደረጉ የተጫዋችች ለውጦች ለቡድኑ ስለጨመሩት ነገር

“የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ችግር አልነበረም ፤ በመጀመሪያው አጋማሽ አብዛኛዎቹ በእራሳቸው ሜዳ ሆነው ነበር የሚጫወቱት መስመር ላይ ያሉ ተጫዋቾችን ስንጠቀም የሚወጡ ሰዎች ነበሩ።ይህን ተጥቀመን ከእነሱ ሰዎች እንዲወጡ ለማድረግ ነበር እቅዳችን የነበረው ፤ ነገርግን መጀመርያ ላይ እንዳልኩህ ማሸነፍ አለብን የሚለው ጉዳይ
ልጆቹ ጋር ቶሎ የመቸኮል ነገር ነበር መሰረታዊው ችግር።”

ስለ ቴዎድሮስ በቀለ

“ጥሩ ነው ፤ ከዚህ በፊት እንደምለው የምንጫወተው ጨዋታ ግልፅ ስለሆነ ስህተቶችን ለማየት ቀላል ነው ከዚህ በፊትም ተናግሪያለሁ ስህተቱ የማይታይ ጨዋታ መጫወት ቀላል ነው አንዳንድ ጊዜ ከኃላ ያሉ ተጫዋቾች ስህተት ጎልቶ የሚታየው ስህተቱን ለማየት ቀላል ስለሆነ ነው ፤ ግን ጥሩ ነው።”

ሊጉ መቋረጥ የሚሰጣቸው ጥቅም ካለ

“ብዙ ስህተቶች አሉ ብዬ አላስም ፤ አንዳንድ ጊዜ የሚፈጠሩ ስህተቶች ዋጋ የሚያስከፍሉ ናቸው። አንደ አጠቃላይ ስተመለከተው ያን ያህል የጎሉ ስህተቶች የሉም ግን የሆነ የሰጠነው ሀሳብ ስላለ ከዛ አንፃር የሚጠበቅ ነገር ስላለ ምናልባት ከዛ አንፃር ይሆናል ስህተቱ ጎልቶ እየተወራ የሚገኘው በመሆኑም የተወሰኑ ነገሮችን ማስተካከል እንዳለብን ይሰማኛል።”

ዘላለም ሽፈራው – ሰበታ ከተማ

ስለጨዋታው

“ከመሀል ሜዳ ጀምሮ ከፍ ያለ ጫና አሳድረን ለመጫወት ፈልግን ነበር እንዳሰብነውም ኳሶችን አግኝተን ነበር የመጠቀም ችግራችን እንዳለ ሆኖ እንዳሰብነው ተጫውተናል ለማለት ያስደፍራል።”

የመስመር አጨዋወታቸው ውጤታማ ያልሆነበት ምክንያት

“ፈጣን እና ጥሩ ግላዊ ክህሎት ያላቸው ተጫዋቾች ብንይዝም መረጋጋት በፍፁም አልቻልንም ፤ ባለፉት ጨዋታዎች ነጥብ መጣላችን የፈጠረው ጫና እንዳለ ሆኖ ነገርግን ለጥረታቸው ግን ሊመሰገኑ ይገባል።”

ሰለ ዘካርያስ ፍቅሬ

“ጥሩ አጥቂ ነው በነበረበት የከፍተኛ ሊግም የምድቡ ከፍተኛ አስቆጣሪ ነበር ዛሬ ላይ ቅን ትንሽ ቀዝቀዝ ብሎ ነበር። ያለቀላቸው አጋጣሚዎችን አምክኗል ለዚህም በርትቶ እንዲሰራ እና እኛም የሚጎለውን ነገር እንዲያሻሽልና ለውጡን በተጨባጭ ማሳየት ይኖርብናል።”

ስለቀጣዩ እረፍት

“በሚገባ እንጠቀማለን አንደኛው ጥቅሙ እንደማንኛውም ቡድን ክፍተቶቻችንን እንድናርም እድል እናገኛለን በተጨማሪም በተሻሉ አቅም ጉዳት ላይ ያሉ ተጫዋቾቻችን ይዘን ዳግም በሙሉ ጉልበት ሊጉን እንድንጀምር ያስችለናል ብዬ አስባለሁ።”