አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | መከላከያ ከ አዲስ አበባ ከተማ

ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አብረው ወደ ሊጉ ያደጉት መከላከያ እና አዲስ አበባ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ተከታዮቹን ወቅታዊ መረጃዎች አሰናድተናል።

ሦስተኛ ተከታታይ ድላቸውን ለማግኘት ሜዳ የደረሱት መከላከያዎች ሰበታ ከተማን አንድ ለምንም ከረቱበት ጨዋታ ላይ አንድ ለውጥ ብቻ አድርገዋል። በዚህም አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ብሩክ ሰሙን በልደቱ ጌታቸው ተክተዋል።

እስካሁን አንድም ጨዋታ ያላሸነፈው አዲስ አበባ ከተማ ከድል ጋር ለመታረቅ ሁለተኛ ሽንፈቱን ካስተናገደበት የአርባምንጩ ጨዋታ ላይ ቢኒያም ጌታቸውን በሪችሞንድ አዶንጎ፣ ዋለልኝ ገብሬን በቻርለስ ሪባኖ፣ ሮቤል ግርማን በሳዲቅ ተማም እንዲሁም ሳሙኤል አስፈሪን በአሰጋኸኝ ጽጥሮስ ተክተዋል። ዋና አሠልጣኙ እስማኤል አቡበከር በክለቡ በተላለፈባቸው እግድ ቡድናቸውን ባይመሩም ምክትል አሠልጣኙ ደምሰው ፍቃዱ ቦታውን ለመሸፈን ተዘጋጅተዋል።

በመዲናዎቹ ሁለት ቡድኖች መሐከል የሚደረገውን ይህን ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው ይመሩታል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ የሚከተከው ነው።

መከላከያ

30 ክሌመንት ቦዬ
11 ዳዊት ማሞ
4 አሌክስ ተሰማ
2 ኢብራሂም ሁሴን
13 ገናናው ረጋሳ
25 ኢማኑኤል ላሪያ
10 አዲሱ አቱላ
19 ልደቱ ጌታቸው
14 ሰመረ ሀፍተይ
5 ግሩም ሀጎስ
18 ኦኩቱ ኢማኑኤል

አዲስ አበባ ከተማ

30 ዳንኤል ተሾመ
14 ልመንህ ታደሰ
6 አሰጋኸኝ ጽጥሮስ
22 ኢያሱ ለገሰ
3 ሳዲቅ ተማም
18 ሙለቀን አዲሱ
20 ቻርለስ ሪባኖ
16 ያሬድ ሀሰን
8 ብዙአየሁ ሰይፉ
10 ፍፁም ጥላሁን
29 ሪችሞንድ አዶንጎ