አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች | አርባምንጭ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና

የሦስተኛ ሳምንት የማሳረጊያ ጨዋታን የተመለከቱ አሁናዊ መረጃዎችን እንድትካፈሉ አዘጋጅተናል።

በሁለተኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታ አዲስ አበባ ከተማን ከመመራት ተነስተው ያሸነፉት አርባምንጭ ከተማዎች ሦስት ነጥብ ካገኙበት ጨዋታ አራት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም አሸናፊ ፊዳ በበርናረድ ኦቼንግ፣ ማርቲን ኦኮሮ በሀቢብ ከማል፣ አብነት ተሾመ በኤሪክ ካፒያቶ እና አሸናፊ ኤሊያስ በእንዳልካቸው መስፍን ተተክተዋል። የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ መሳይ ተፈሪ ደግሞ ለጨዋታው በተለየ መልኩ መዘጋጀታቸውን እና ጨዋታውን ለማሸነፍ ጥሩ እና በቂ ዝግጅት እንዳደረጉ በቅድመ ጨዋታ አስተያየታቸው ተናግረዋል።

በባህር ዳር ከተማ ባለቀ ሰዓት በተቆጠረ ግብ የተረቱት ሀዲያ ሆሳዕናዎች ደግሞ ሁለት ለውጦችን አድርገዋል። በዚህም የግብ ብረቶቹ መካከል የሚቆመውን መሳይ አያኖ በስሆሆ ሜንሳ እንዲሁም የመስመር ተከላካዩን እያሱ ታምሩን በሄኖክ አርፊጮ ለውጠዋል። የቡድኑ አሠልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ደግሞ ከዚህ በፊት ባደረጉት ሁለት ጨዋታዎች ካሳዩት እንቅስቃሴ እና ካስመዘገቡት ውጤት የተሻለ ነገር ለማግኘት ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ጨዋታውን ፌዴራል ዳኛ ሄሚክ አክሊሉ በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ የሚከተለው ነው።

አርባምንጭ ከተማ

1 ሳምሶን አሰፋ
14 ወርቅይታደሰ አበበ
15 በርናርድ ኦቼንግ
5 አንድነት አዳነ
2 ተካልኝ ደጀኔ
23 ሀቢብ ከማል
20 እንዳልካቸው መስፍን
21 አንዱአለም አስናቀ
22 ፀጋዬ አበራ
26 ኤሪክ ካፒያቶ
9 በላይ ገዛኸኝ

ሀዲያ ሆሳዕና

1 ሶሆሆ ሜንሳ
12 ብርሀኑ በቀለ
16 ፍሬዘር ካሣ
6 ኤሊያስ አታሮ
17 ሄኖክ አርፊጮ
21 ተስፋዬ አለባቸው
8 ሳምሶን ጥላሁን
10 ፍቅረየሱስ ተወልደብርሀን
25 ሀብታሙ ታደሰ
31 ዑመድ ዑኩሪ
9 ባዬ ገዛኸኝ